ወደ አምላክ ይበልጥ መቅረብ የሚቻለው እንዴት ነው?
ወደ አምላክ ይበልጥ መቅረብ የሚቻለው እንዴት ነው?
በርካታ ሰዎች ወደ ይሖዋ ቅረብ የሚል ርዕስ ያለውን መጽሐፍ በማንበብ የተለያየ ሐሳብ ሰንዝረዋል። መጽሐፉን ያነበበች አንዲት ሴት እንዲህ ብላ ጽፋለች:- “መጽሐፉን ገና አንብቤ መጨረሴ ነው፤ ከዚህ በፊት የአሁኑን ያህል ልቤ በጥልቅ ተነክቶ አያውቅም። በእውነትም ይሖዋ አፍቃሪ፣ ተንከባካቢ፣ ደግና አሳቢ አባት መሆኑን ለሚገልጸው ማሳሰቢያ ሁሉ አመሰግናለሁ።”
ሌላ ሴት ደግሞ “መጽሐፉን ማንበቤ አባቴን ይሖዋን ከበፊቱ ይበልጥ እንዳውቀው ይኸውም ጥልቅ ስለሆነው ሐሳቡና ለሁላችንም ስላለው ታላቅ የፍቅር ስሜት እንድገነዘብ አስችሎኛል። መጽሐፉን ማንበብ፣ የሚያንጸባርቅ ውብ አልማዝ ከማግኘትና ቀስ እያሉ በማገላበጥ ሁሉንም ገጽታውን ከመመርመር ጋር ይመሳሰላል፤ እያንዳንዱ አዲስ ምዕራፍ ቀደም ካለው ምዕራፍ ይበልጥ አስደናቂ ይዘት አለው” በማለት የተሰማትን ገልጻለች።
አንዲት ሌላ ሴትም ስሜቷን እንዲህ በማለት ጠቅሳለች:- “ወደ ይሖዋ ቅረብ የሚለውን መጽሐፍ አንብቤ መጨረሴ ነው። በአድናቆትና በፍቅር ተውጬ ስለነበር የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች ላይ እስከምደርስ ድረስ ለበርካታ ጊዜያት ቆም ብዬ ጸልያለሁ። ለይሖዋ ያለኝ ፍቅርና አድናቆት በእጅጉ ጨምሯል!”
እርስዎም ይህን ባለ 320 ገጽ መጽሐፍ ቢያነቡ ተመሳሳይ ስሜት እንደሚሰማዎት እናምናለን። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ።
□ ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።