በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በቤተሰብ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮች የሚሆን እርዳታ

በቤተሰብ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮች የሚሆን እርዳታ

በቤተሰብ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮች የሚሆን እርዳታ

በሜክሲኮ፣ ቬራክሩዝ የምትኖር አንዲት ሴት በቤተሰቧ ውስጥ የተከሰተውን ችግር የሚዳስስ ንቁ! መጽሔት ተበረከተላት። “መጽሔቱ እኔን የሚመለከት ርዕሰ ጉዳይ ስለያዘ ቀልቤን ሳበው” በማለት ጽፋለች። ለይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የጻፈችው ደብዳቤ በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “መጽሔቱ ለእኔ፣ ለባለቤቴና ለልጆቼ የሚሆን ጠቃሚ ሐሳብ ይዟል።”

አክላም “ስለ ይሖዋ ምሥክሮች በደንብ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ እንዲሁም በአቅራቢያዬ የሚገኘውን ጉባኤ አድራሻ ማግኘት እፈልጋለሁ። ከአምላክ ጋር ከአሁኑ የበለጠ መቀራረብ እንዳለብን ስለማምን በስብሰባው ላይ ከነቤተሰቤ የመገኘት ፍላጎት አለኝ” ብላለች። ሴትየዋ በንቁ! መጽሔቱ የመጨረሻ ገጽ ላይ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ስላለው መጽሐፍ የተሰጠው መግለጫ ከፍተኛ ጉጉት ስላሳደረባት መጽሐፉ እንዲላክላት ጠየቀች።

መጽሐፉ ለባሎች፣ ለሚስቶች፣ ለወላጆች፣ ለልጆችና ለአያቶች፣ አዎን ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የሚጠቅም ሐሳብ ይዟል። ትምህርት ሰጪ ከሆኑት ምዕራፎች መካከል “ልጆቻችሁን ከሕፃንነታቸው ጀምሮ አሠልጥኗቸው፣” “በጉርምስና ዕድሜ የሚገኙ ልጆቻችሁ በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እርዷቸው፣” “ቤተሰባችሁን ጎጂ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ጠብቁ” እና “በቤተሰባችሁ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን አድርጉ” የሚሉት ይገኙበታል።

እርስዎም ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።