በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዚህ ልጅ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ መጽሐፍ

በዚህ ልጅ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ መጽሐፍ

በዚህ ልጅ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ መጽሐፍ

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ፔንሲልቬኒያ ውስጥ በምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ የሚኖር ሴቪየን የተባለ ልጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ ስለተባለው መጽሐፍ ያለውን አድናቆት ለመግለጽ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ደብዳቤ ጽፎ ነበር። ደብዳቤውን የጻፈው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጹ ሰዎችና ክንውኖች የሚናገረውን በሥዕል የተደገፈ መጽሐፍ አንብቦ እንደጨረሰ መሆኑን ተናግሯል።

ለመጽሐፉ አሳታሚዎች እንዲህ ሲል ጽፏል:- “እንደ እኔ ያሉ ትንንሽ ልጆች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ እንዲያውቁ ማበረታታችሁን ለመቀጠል ይህንን መጽሐፍ ማተማችሁን መቀጠል ያለባችሁ ይመስለኛል።

“ይህ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ የያዘው ነገር ሁሉ ትክክል መሆኑን እንዲሁም የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ ተስፋ እንዲኖረን እኛን ለማስተማር ተብሎ የተጻፈ መሆኑን እንዳውቅ አስችሎኛል።

“ለእኛ ለልጆች ባታስቡልንና ትምህርቱ በጥሩ ሁኔታ እንዲገባን መጽሐፉን ቀለል ባለ መንገድ ባታዘጋጁልን ኖሮ ይህንን እውቀት ማግኘት ባልቻልኩ ነበር።”

ልጅዎን ለማስተማር ምን ያደረጉት ጥረት አለ? የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለው ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ይህ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጹ ሰዎችና ክንውኖች የሚገልጹ 116 ታሪኮችን ይዟል። ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ከሞሉ በኋላ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ መጥታችሁ አነጋግሩኝ።