በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘የሚያስተምሩኝ ፕሮፌሰሮች በጣም ተደስተዋል’

‘የሚያስተምሩኝ ፕሮፌሰሮች በጣም ተደስተዋል’

‘የሚያስተምሩኝ ፕሮፌሰሮች በጣም ተደስተዋል’

ለንቁ! መጽሔት አዘጋጆች በላከው ደብዳቤ ላይ እንዲህ በማለት የጻፈው በጆርጂያ አገር በትቢሊሲ ግዛት የሕክምና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማር የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው። ደብዳቤውን እንዲጽፍ ያነሳሳው ምን ነበር?

“ከ1998 ጀምሮ መጽሔቶቻችሁን አነብባለሁ። . . . ለትምህርቴ ትልቅ እገዛ ያደርጉልኛል። በመጽሔቶቹ ላይ የሚወጡት ርዕሶች ሁልጊዜ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ የሚያቀርቡት መረጃም አስተማማኝ ነው። በቅርቡ ‘ማባቀል (cloning) እና የሰው ሠራሽ ሕዋስ ዓይነቶች’ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ለማዘጋጀት በኅዳር 22, 2002 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ላይ ከወጣው “ሰው ሠራሽ ሕዋሳት—ሳይንስ አቅጣጫውን እየሳተ ነው?” የሚል ርዕስ የተወሰዱ ሐሳቦችን ተጠቅሜ ነበር። የሚያስተምሩኝ ፕሮፌሰሮች በጣም የተደሰቱ ሲሆን ከፍተኛውን ውጤትም አግኝቻለሁ።

“እንደነዚህ ያሉ ትኩረት የሚስቡ ርዕሰ ጉዳዮችን በተለይም ሕክምናን የሚዳስሱ ርዕሶችን የምታወጡ መሆኑ በጣም ያስደስተኛል። እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ የይሖዋ ምሥክሮች ባንሆንም በዙሪያችን ስላለው ዓለም ያለንን ግንዛቤ ስለሚያሰፉልን መጽሔቶቻችሁን በጣም እንወዳቸዋለን።”

መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ጤንነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮችን እንደያዘ ሲያውቁ ይገረሙ ይሆናል። ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ይህን እውነታ ጥሩ አድርጎ ያጎላል። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህ ብሮሹር እንዲላክልዎ መጠየቅ ይችላሉ።

ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።