በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለወጣቶች የሚሆን ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ የመማሪያ መጽሐፍ

ለወጣቶች የሚሆን ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ የመማሪያ መጽሐፍ

ለወጣቶች የሚሆን ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ የመማሪያ መጽሐፍ

በኬንያ ሊሙሩ ከተማ የሚገኘው ቲጎኒ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር በዚያ አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ደብዳቤ በመጻፍ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለው መጽሐፍ እንዲላክላቸው ጠየቁ። ዳይሬክተሩ በደብዳቤው ላይ እንዲህ ብለዋል:- “እንደምታውቁት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ማስተማር ፈታኝ ሊሆን ይችላል። የዚህ መጽሐፍ ሁለት ቅጂዎች ያሉን ሲሆን መምህራኑንም ሆነ ተማሪዎቹን ጠቅመዋቸዋል። መጽሐፉ በውስጡ በቂ የሆነ መረጃ የያዘ ከመሆኑም በላይ የእኛን የአስተማሪዎችንም ሆነ የወጣቶቻችንን ፍላጎት የሚያሟላ ነው።”

ዳይሬክተሩ በመቀጠልም:- “[የትምህርት ቤቱ] አስተዳደር ይህን ጠቃሚ መጽሐፍ በትምህርት ቤታችን ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች ለማስተማር ይፈልጋል።” ካሉ በኋላ አክለውም “ልጃገረዶቹ መጽሐፉን በጣም ወደውታል። ወላጆችም ቢሆኑ ልጆቻቸውን ለመርዳት በሚደረገው ጥረት ተደስተዋል። ለአሁኑ የመጽሐፉን 25 ቅጂዎች ብትልኩልን በቂ የሚሆን ይመስለናል” በማለት ደብዳቤያቸውን ደምድመዋል።

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተባለው መጽሐፍ የወጣቶችን አመለካከትና ስሜት ለመረዳት የሚያስችል ከመሆኑም በላይ እንደሚከተሉት ባሉ ርዕሶች ዙሪያ ጠቃሚ ሐሳብ ይዟል:- “ወላጆቼ ተጨማሪ ነፃነት እንዲሰጡኝ ለማድረግ የምችለው እንዴት ነው?፣” “የወላጆቼን ቤት ትቼ መውጣት ይኖርብኛልን?፣” “እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?፣” “ምን ዓይነት የሥራ መስክ መምረጥ ይሻለኛል?፣” “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?” እና “እውነተኛ ፍቅር መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?”

ከላይ የተገለጹት ርዕሶች መጽሐፉ ከያዛቸው ምዕራፎች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ይህ መጽሐፍ በ39 ምዕራፎቹ ውስጥ ሌሎች ርዕሶችንም ይዟል። እርስዎም የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።