በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሃይማኖቶች የበዙት ለምንድን ነው?

ሃይማኖቶች የበዙት ለምንድን ነው?

ሃይማኖቶች የበዙት ለምንድን ነው?

አንዲት ሴት በአውቶቡስ ስትጓዝ ከአንድ የይሖዋ ምሥክር ጋር ስላደረገችው ውይይት የሚገልጽ ደብዳቤ በጓቲማላ ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ጻፈች። በደብዳቤዋ ላይ “ብዙ ሃይማኖቶች የኖሩት ለምን እንደሆነ ተነጋገርን” ካለች በኋላ ምሥክሩ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የሚለውን ብሮሹር አውጥቶ “እውነተኛውን ሃይማኖት ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ እንዳሳያት ገለጸች። “ርዕሱ በጣም አስገረመኝ፤ አንድ የእውነተኛው አምልኮ ቡድን መኖር እንዳለበት እስከዚያን ጊዜ ድረስ አላውቅም ነበር” ስትል ጽፋለች።

ብሮሹሩን ስታነበው ስሜቷ በጥልቅ ተነካ። በመሆኑም እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “በብሮሹሩ ውስጥ የሰፈረው ሐሳብ እውነት ለመሆኑ እርግጠኛ ነኝ። ይህን ደብዳቤ ልጽፍላችሁ የተነሳሳሁትም በብሮሹሩ ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንድማር ልትረዱኝ ትችሉ እንደሆነ ልጠይቃችሁ ነው።”

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር 32 ገጾች ያሉት ሲሆን መጠኑ ይህንን መጽሔት ያክላል። ከላይ ከተገለጸው ጥያቄ በተጨማሪ ብሮሹሩ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥያቄዎች መልስ ይዟል:-

▪ እውነተኛው አምላክ ማን ነው?

▪ አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

▪ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

▪ አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ሊኖርህ የሚችለው እንዴት ነው?

እርስዎም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር በማንበብ ይጠቀሙ ይሆናል። ይህን ብሮሹር ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።