በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከንቁ! ላይ ያገኘችው እውቀት

ከንቁ! ላይ ያገኘችው እውቀት

ከንቁ! ላይ ያገኘችው እውቀት

በሜክሲኮ፣ ቬራክሩዝ የምትኖረው የ8 ዓመቷ ፔርላ የ2ኛ ክፍል ተማሪ ናት። አንድ ቀን አስተማሪዋ ዓሣ ነባሪ ምን ያህል ርዝመት እንዳለው ጠየቀቻቸው። መጀመሪያ ላይ መልስ የሰጠ አልነበረም። ከዚያም ፔርላ እጅዋን አወጣችና “ግራጫው ዓሣ ነባሪ 14 ሜትር ርዝመትና 16,000 ኪሎ ግራም ክብደት አለው” ብላ ተናገረች።

አስተማሪዋም በመገረም “እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?” ብላ ጠየቀቻት።

“ከንቁ! መጽሔት ላይ” ብላ ከመለሰች በኋላ “ከፈለግሽ ላሳይሽ እችላለሁ” አለቻት። ፔርላ ለሌሎች ለማሳየት ብላ በቅርብ ጊዜ የወጡትን የንቁ! መጽሔት እትሞች በትምህርት ቤት ቦርሳዋ ውስጥ የመያዝ ልማድ ነበራት። እንደ አጋጣሚ ሆኖ “ግራጫ ዓሣ ነባሪዎችን የማየት አጋጣሚ ያገኘንበት የማይረሳ ጊዜ” የሚል ርዕስ ያለውን የመስከረም 8, 2003 እትም ይዛ ነበር።

የፔርላ አስተማሪ የመጽሔቱን አንድ ቅጂ በማግኘቷ ደስ አላት። መጽሔቱን ያነበበች ከመሆኑም ሌላ ለራሷ ማስቀረት ፈለገች። ሌሎች ተማሪዎችም መጽሔቱን ማግኘት ስለፈለጉ ዘጠኝ ለሚያህሉት አመጣችላቸው። ፔርላ ለመምህሯ በየሁለት ሳምንቱ ንቁ! መጽሔት የምትወስድላት ሲሆን እርሷም በጣም ታመሰግናታለች።

ከዚህ በኋላ፣ ብዙም ሳይቆይ ፔርላ የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ ተካፈለች። ፔርላ ወደ ስብሰባው ከመሄዷ በፊት መምህሯ ከስብሰባው አንድ ስጦታ ይዛላት ብትመጣ ደስ እንደሚላት ነገረቻት። ስለዚህም ፔርላ በዚያ ስብሰባ ላይ ወጥቶ የነበረውን ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ አመጣችላት።

ቀጥሎም መምህሯ ለተወሰኑ ተማሪዎቿ “ፔርላ ትምህርቷን በቁም ነገር የምትከታተል ከመሆኑም በተጨማሪ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች የያዙ መጻሕፍትን በማንበብና ለእኛም በመንገር ረገድ ጥሩ ምሳሌ የምትሆን ናት” አለቻቸው።