በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአምላክ ስም መጠቀም ይገባናል?

በአምላክ ስም መጠቀም ይገባናል?

በአምላክ ስም መጠቀም ይገባናል?

በ1902 ዘ ፕሪስባይቴሪያን ኤንድ ሪፎርምድ ሪቪው የተባለው መጽሔት በ1901 የታተመውን የአሜሪካን ስታንዳርድ ቨርሽን መውጣት አስመልክቶ አንድ ሪፖርት አቅርቦ ነበር። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በ17ኛው ክፍለ ዘመን ታትሞ ከነበረው የኪንግ ጀምስ ቨርሽን ተሻሽሎ የቀረበ ነው። መጽሔቱ በእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጂሆቫ (በአማርኛችን ይሖዋ) የሚለውን የአምላክ ስም በተደጋጋሚ መጠቀም ተገቢ በመሆኑ ላይ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እንደሚከተለው ብሏል:-

“ስሙን የመጠቀሙ ትክክለኝነት ላይ የአስተሳሰብ ልዩነት መኖሩ ሊገባን አልቻለም። ይህ የጌታ የግል ስም ነው፤ ሕዝቦቹ እንዲያውቁት የመረጠውም በዚህ ስም ነው። የግል ስሙን በሌሎች የማዕረግ ስሞች መተካት እጅግ ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚያስከትል ይሰማናል። የስሙ ትክክለኛ አጠራር አወዛጋቢ መሆኑ አይካድም፤ እንዲሁም ማናችንም ብንሆን ‘ጂሆቫ’ የሚለው አጠራር ትክክል ነው ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር አንችልም። ያም ሆኖ ግን በእንግሊዝኛ አንባቢዎች ዘንድ የትክክለኛውን አጠራር ያህል ዋጋ አለው። ስለዚህ ይህን ስም ያህዌ በሚለውም ይሁን ምሑራን ይነስም ይብዛ ትክክለኛ ናቸው ብለው በሚያምኑባቸው ሌሎች አጠራሮች መተካት ለጥቃቅን ጉዳዮች ከልክ በላይ መጨነቅ ይሆናል። ብሉይ ኪዳንን የሚያነብ አንድ እንግሊዝኛ አንባቢ ሰፊ ተቀባይነት ባለው በዚህ ትርጉም ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ጂሆቫ’ የሚለውን ስም መመልከቱ እንዲሁም ‘ጂሆቫ’ በሕዝቦቹ ዘንድ ምን ቦታ እንዳለውና ለእነርሱ ምን እንደፈጸመላቸው መረዳቱ የሚያስገኝለት ጥቅም እንዲህ ቀላል እንዳልሆነ እንገነዘባለን።”

ሌሎች በርካታ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የአምላክን ስም ለመጻፍ “ጂሆቫ” የሚለውን ወይም ሌላ ዓይነት አጠራር ይጠቀማሉ። በተመሳሳይም፣ የአምላክ የግል ስም በሌሎች ቋንቋዎች በተዘጋጁ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ይገኛል፤ በዚህ ገጽ ላይ የሚታዩት ለአብነት ያህል የቀረቡ ናቸው። አምላክ ለሙሴ ይሖዋ የሚለውን ስሙን በተመለከተ “ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው” ሲል ነግሮታል። ስለሆነም በዛሬው ጊዜ በስሙ መጠቀም ተገቢ መሆኑ አያጠያይቅም።—ዘፀአት 3:13-15

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መዝሙር 83:18 በተለያዩ ቋንቋዎች ሲጻፍ

ጾንጋ

ሾና

በቬትናም ቋንቋ

ስፓንኛ

ሂንዲ

ተጋሎግ

እንግሊዝኛ