በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘በዚህ ልትኮራ ይገባሃል’

‘በዚህ ልትኮራ ይገባሃል’

‘በዚህ ልትኮራ ይገባሃል’

እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች ሐቀኝነት ያለውን ጥቅም ይገነዘባሉ። ይህንን ባሕርይ እንዲያሳዩ የሚገፋፋቸውም ለፈጣሪያቸው ያላቸው ፍቅር ነው። እስቲ ላሳሮ ያደረገውን ነገር እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ከተወሰነ ጊዜ በፊት በሜክሲኮ፣ ዋቱልኮ በሚገኝ አንድ ሆቴል ተቀጥሮ ሲሠራ በእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ 70 ዶላር ወድቆ አገኘ። ወዲያውኑ፣ ገንዘቡን በወቅቱ በሥራ ላይ ለሚገኘው ሥራ አስኪያጅ አስረከበ። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ በመታጠቢያ ክፍል ውስጥ አንድ የኪስ ቦርሳ አገኘ። ይህንንም ወስዶ በእንግዳ መቀበያው ክፍል ለሚሠራው ሰው አስረከበ። ቦርሳው የጠፋባት ሴት ገንዘቧን ስታገኝ የተደሰተች ከመሆኑም ሌላ አድራጎቱ አስገረማት።

ላሳሮ ያደረገውን ነገር ዋና ሥራ አስኪያጁ ሲሰማ ገንዘቡንም ሆነ ቦርሳውን ለመመለስ ያነሳሳው ምን እንደሆነ ጠየቀው። ላሳሮ ሥነ ምግባርን አስመልክቶ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማረው ትምህርት የራሱ ያልሆነን ነገር እንዳይወስድ እንደከለከለው ነገረው። ዋና ሥራ አስኪያጁ ለላሳሮ በጻፈለት የምስጋና ደብዳቤ ላይ እንዲህ አለው:- “በዛሬው ጊዜ ከፍተኛ የሥራ ምግባር መሥፈርቶችን የሚጠብቁ ሰዎች ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ፀባይህን እናደንቃለን። ለሥራ ባልደረቦችህ ምሳሌ የምትሆን ጨዋ ሰው መሆንህን አስመስክረሃል። አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በዚህ ጉዳይ ልትኮሩ ይገባችኋል።” በዚህም ምክንያት ላሳሮ የወሩ ምርጥ ሠራተኛ ተብሎ ተሰየመ።

አንዳንድ የሥራ ባልደረቦቹ ቦርሳውንም ሆነ ገንዘቡን መመለሱ ትክክል አይደለም ብለው አስበው ነበር። ይሁንና ቀጣሪያቸው የሰጠውን ምላሽ በተመለከቱበት ወቅት የሥነ ምግባር አቋሙን ባለመጣሱ መደሰታቸውን ገለጹለት።

መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ታማኝ ተከታዮች ‘ለሰው ሁሉ መልካም እንዲያደርጉ’ እንዲሁም “በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር” እንዲኖሩ ያሳስባቸዋል። (ገላትያ 6:10፤ ዕብራውያን 13:18) በእርግጥም ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን በሐቀኝነት መመላለሳችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ቀጥተኛና ጻድቅ” ተብሎ ለተገለጸው ለይሖዋ አምላክ ክብር ያመጣለታል።—ዘዳግም 32:4