በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዘንድሮስ ምን አዲስ ፊልም ይወጣ ይሆን?

ዘንድሮስ ምን አዲስ ፊልም ይወጣ ይሆን?

ዘንድሮስ ምን አዲስ ፊልም ይወጣ ይሆን?

የክረምቱ ወራት አልፎ በጋው ሲገባ የሚታይህ ነገር ምንድን ነው? የአየሩ ሁኔታ ሞቅ ሲል ሜዳ ወጥተህ መጫወት ወይም ወደ ባሕር ዳርቻ አሊያም ወደ መናፈሻ ቦታዎች ሄደህ መዝናናት ሊያምርህ ይችላል።

ይሁን እንጂ በፊልም ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ብዙዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየቤታቸውና በየፊልም ቤቶች ሆነው በርካታ ሰዓታት ፊልም እያዩ እንዲያሳልፉ ይመኛሉ። በዩናይትድ ስቴትስ ብቻ ከ35,000 ያላነሱ የፊልም ማሳያ ቦታዎች ያሉ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፊልም ቲኬቶች ሽያጭ ከሚገኘው ትርፍ 40 በመቶ ያህሉ የሚገኘው በበጋዎቹ ወራት ነው። * የሙቪላይን መጽሔት ባልደረባ የሆኑት ሄይዲ ፓርከር ሁኔታው “ቸርቻሪዎች የገናን ሰሞን በናፍቆት ከመጠበቃቸው ጋር ተመሳሳይ ነው” ብለዋል።

ድሮ ድሮ ሁኔታው እንዲህ አልነበረም። የበጋው ወራት በዩናይትድ ስቴትስ የፊልም ቤቶች ገበያ ቀዝቀዝ የሚልበት ጊዜ ስለሆነ ብዙዎቹ ፕሮግራሞቻቸውን ለመቀነስ ወይም ከነጭራሹ ለመዝጋት ይገደዱ ነበር። በ1970ዎቹ ዓመታት አጋማሽ ላይ ግን በአየር ማቀዝቀዣዎች መስፋፋት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የበጋውን ሙቀት ለመሸሽ ሲሉ ወደ ፊልም ቤቶች መጉረፍ ጀመሩ። ትምህርት ቤት ሲዘጋ ዕረፍት ላይ የሚሆኑ ልጆችም ጥሩ ትርፍ ማግበስበሻ ሊሆኑ መቻላቸው የፊልም ሠሪዎችን ትኩረት ሳበ። ብዙም ሳይቆይ በጣም ብዙ ተመልካች ያተረፉ የበጋ ፊልሞች መውጣት ጀመሩ። ይህም ወደፊት እንደምንመለከተው በፊልሞች አሠራርም ሆነ አሻሻጥ ላይ ትልቅ ለውጥ አስከተለ።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.3 በዩናይትድ ስቴትስ የበጋ የፊልም ወቅት የሚጀምረው በግንቦት ሲሆን እስከ መስከረም ይዘልቃል።