በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለጥያቄዎቻቸው መልስ ማግኘት የሚፈልጉ ወጣቶች

ለጥያቄዎቻቸው መልስ ማግኘት የሚፈልጉ ወጣቶች

ለጥያቄዎቻቸው መልስ ማግኘት የሚፈልጉ ወጣቶች

በ2002 በቶሮንቶ፣ ካናዳ 17ኛው የካቶሊክ የዓለም ወጣቶች ቀን የተከበረ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ከዓለም ዙሪያ ተሰባስበው ነበር። የይሖዋ ምሥክሮች የዚህ ክንውን ተካፋይ ባይሆኑም እንኳ ብዙ ወጣቶች ወደ ከተማው እንደሚመጡ ጠብቀው ነበር። ለዚህ ክንውን አስቀድመው የተዘጋጁት እንዴት ነበር? በአንደኛው መቶ ዘመን ይኖሩ እንደነበሩት ክርስቲያኖች አጋጣሚውን ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች ለመናገር ተጠቅመውበታል።—የሐዋርያት ሥራ 16:12, 13

ምሥክሮቹ ወጣቶቹ ላሳዩት መንፈሳዊ ፍላጎት ምስጋናቸውን ገለጹላቸው። ይህም ከብዙዎች ጋር በቅዱስ ጽሑፉ ላይ የተመሠረተ ወዳጃዊ ውይይት ለማድረግ አስችሏቸዋል። አንዲት ምሥክር የዓለም ወጣቶች ቀንን እንዳሰበችው አግኝታው እንደሆነ አንዲትን ወጣት ስትጠይቃት “እስካሁን ሙዚቃና ዳንስ ከመኖሩ ሌላ እምነቴን የሚገነባ ምንም ነገር አላገኘሁም” ብላ መለሰችላት።

ከዚያም ምሥክሯ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር አበረከተችላት። ብሮሹሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አስመልክተው ከሚጠይቋቸው በርካታ ጥያቄዎች መካከል “መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው?” እንዲሁም “የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ከመጀመሪያው ቅጂ እንዳልተለወጠ እንዴት እናውቃለን?” ለሚሉት መልስ እንደሚሰጥ ነገረቻት።

ወጣቷም እንዲህ ስትል መለሰች:- “በአሁኑ ወቅት በሕይወቴ ውስጥ ግራ የሚያጋቡኝ ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው። ለጥያቄዎቼ መልስ ለማግኘት አሁኑኑ ማንበብ አለብኝ። ምናልባት ከዚህ ጉዞዬ የማገኘው በጣም ጠቃሚ ነገር ይህ ሊሆን ይችላል።”

ይህ ሁኔታ የይሖዋ ምሥክሮች የካቶሊክ የዓለም ወጣቶች ቀንን ለማክበር ከመጡት እንግዶች ጋር ካደረጓቸው በርካታ ውይይቶች መካከል አንዱ ነበር። እርስዎም ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ለማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።