በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በሀብት የተከፋፈለ ዓለም

በሀብት የተከፋፈለ ዓለም

በሀብት የተከፋፈለ ዓለም

በ20ኛው መቶ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ዓለም ወደ ቀዝቃዛው ጦርነት የገባ ከመሆኑም በላይ በሦስት የፖለቲካ ጎራዎች ተከፍሎ ነበር። አንደኛው በሶቪዬት ኅብረት የሚመራው የኮሚኒስቱ ዓለም ሲሆን ሌላው በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው የካፒታሊስት ጎራ ነው፤ እነዚህ ሁለት ጎራዎች በመካከላቸው ከተደነቀረው የብረት መጋረጃ አሻግረው እርስ በርስ በጠላትነት ይተያዩ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ከሁለቱ ጎራዎች ጋር ያልወገኑት ብሔራት ሦስተኛው ዓለም የሚባል ቡድን መሠረቱ።

የኋላ ኋላ “ሦስተኛው ዓለም” የሚለው ስያሜ አሉታዊ ትርጓሜ እየያዘ በመሄዱ “ያላደጉ አገሮች” በሚል መጠሪያ ተተካ። ይሁንና ይህም ቢሆን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ አሉታዊ ስሜት ማስተጋባቱ አልቀረም። በመሆኑም የኢኮኖሚ ጠበብቶች “በማደግ ላይ ያሉ አገሮች” የሚለውን ስያሜ መጠቀም ጀመሩ። ስለዚህ ስያሜው በአገሮች መካከል ያለውን የፖለቲካ ልዩነት የሚጠቁም መሆኑ ቀርቶ ኢኮኖሚያዊ ደረጃቸውን የሚያመለክት ሆነ።

በዚህ በ21ኛው መቶ ዘመን፣ ዓለም ከላይ በተጠቀሱት ሦስት የፖለቲካ ጎራዎች መከፈሏ አክትሟል። ይሁንና አሁንም ቢሆን በማደግ ላይ ባሉት እና ባደጉት አገሮች መካከል የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ ልዩነት በግልጽ ይታያል። ዛሬም፣ ባለጸጋ ከሆኑ አገሮች የሚመጡ ቱሪስቶች ለቤተሰባቸው የዕለት ጉርስ ለማግኘት ደፋ ቀና ከሚሉ ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ሰዎች ጋር ይገናኛሉ።

በመሆኑም፣ የሚከተለው ጥያቄ መነሳቱ የተገባ ነው:- ዓለም ወደፊትም ቢሆን በኢኮኖሚ እንደተከፋፈለ ይቀጥላል ወይስ በድህነት የሚማቅቁ ሰዎች ከሀብታሞች ጋር በኑሮ እኩል የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Qilai Shen/Panos Pictures