በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ በእርግጥ ስለ እኛ ያስባል?

አምላክ በእርግጥ ስለ እኛ ያስባል?

አምላክ በእርግጥ ስለ እኛ ያስባል?

▪ብዙዎች፣ ‘አምላክ ቢኖር ኖሮ ሰዎች እንዲህ ሲሰቃዩ ዝም ብሎ አይመለከትም ነበር’ ብለው ያስባሉ። አንዳንዶች “አምላክ ካለ በችግራችን ጊዜ ለምን አልደረሰልንም?” ብለው መጠየቃቸው የተለመደ ነው። በታሪክ ዘመናት ሁሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከባድ መከራ የተፈራረቀባቸው ከመሆኑም በላይ በደረሰባቸው ሥቃይ የተነሳ የሞቱም አሉ።

በሌላ በኩል ሕይወት ያላቸው ነገሮች አስደናቂ ሥርዓትና ንድፍ ያላቸው መሆኑ አሳቢ የሆነ ፈጣሪ መኖሩን በግልጽ ያሳያል። ታዲያ ስለ እኛ የሚያስብ አምላክ ካለ እንደነዚህ ያሉ አሰቃቂ ችግሮች ሲደርሱብን ዝም ብሎ የሚመለከተው ለምንድን ነው? አምላክን በተገቢው ሁኔታ ማገልገል እንድንችል ለዚህ አንገብጋቢ ጥያቄ መልስ ማግኘት ይኖርብናል። መልሱን ከየት ማግኘት እንችል ይሆን?

አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የሚለውን ብሮሹር አግኝተው እንዲያነቡ እንጋብዝዎታለን። “አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደበት ምክንያት” እና “የዓመፅ ውጤት ምን ሆነ?” የሚሉትን ክፍሎች በሚገባ ቢያነቡ አጥጋቢ መልስ እንደሚያገኙ እናምናለን።

ይህን ብሮሹር ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን? የሚለውን ብሮሹር እፈልጋለሁ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።