በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ጥሩ ትዳር ለመመሥረት ያስችላል?

ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ጥሩ ትዳር ለመመሥረት ያስችላል?

ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ጥሩ ትዳር ለመመሥረት ያስችላል?

ጆርናል ኦቭ ሜሬጅ ኤንድ ፋምሊ የተባለ መጽሔት ወንድና ሴት ጋብቻ ሳይፈጽሙ አብረው መኖራቸው “በዓለም ዙሪያ ባሉ ዘመናዊ ኅብረተሰቦች ዘንድ እየተለመደ መጥቷል” በማለት ዘግቧል። አክሎም “ሳይጋቡ አብረው ከሚኖሩት ውስጥ ግማሽ የሚያህሉት፣ አብረው መኖራቸው ቢጋቡ ተስማምተው መኖር እንደሚችሉና እንደማይችሉ አስቀድመው ለመገምገም እንደሚረዳቸው ያምናሉ” ብሏል። ይህ እውነት ከሆነ ሳይጋቡ አብሮ መኖር ከተጋቡ በኋላ “አለመስማማትን ማስወገድና ጋብቻው ዘላቂ እንዲሆን ማስቻል አለበት” በማለት መጽሔቱ ተናግሯል።

መጽሔቱ ስለ ውጤቱ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “እውነታው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። ከመጋባታቸው በፊት አብረው ኖረው ጋብቻ የፈጸሙ ሰዎች በትዳራቸው እምብዛም እንደማይደሰቱ፣ ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ብዙ ጊዜ አብረው እንደማያሳልፉ፣ ከባድ አለመስማማት እንደሚያጋጥማቸው፣ የትዳር ጓደኛቸው ብዙም ድጋፍ እንደማያደርግላቸው፣ ችግሮቻቸውን በቀላሉ መፍታት እንደማይችሉ [እና] ከጋብቻ ጋር የተያያዙ ሌሎች በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸው ይናገራሉ . . . ከዚህም በላይ ሳይጋቡ አብረው ከኖሩ በኋላ የተጋቡ ባለ ትዳሮች በቀጥታ ወደ ትዳር ዓለም ከገቡ ሰዎች ይልቅ የመፋታታቸው አጋጣሚ በጣም ሰፊ ነው።”

ሰዎች በጣም ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡት ነገር በተቃራኒው ጎጂ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያሳያል። ይህ እውነታ ኤርምያስ 10:23 እንደሚለው ሰው ‘አካሄዱን በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል’ ያረጋግጣል። ጋብቻን በተመለከተ የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልካም ምክር መከተል እንዴት ያለ ጥበብ ነው! (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ለምሳሌ ያህል በተጋቢዎች መሃል ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”—ዘፍጥረት 2:24፤ ማቴዎስ 19:5

ጉድለት ካለውና ተለዋዋጭ ከሆነው የሰው ልጆች አስተሳሰብ ይልቅ መለኮታዊውን መመሪያ መቀበል እውነተኛ ደስታ ያለበት ዘላቂ ትዳር ለመመሥረት ያስችላል።—ምሳሌ 3:5, 6