በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመኖሪያ ቤት እጦት—ዓለም አቀፍ ችግር

የመኖሪያ ቤት እጦት—ዓለም አቀፍ ችግር

የመኖሪያ ቤት እጦት—ዓለም አቀፍ ችግር

ፖላንድ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

“የሚከረፉ፣ ቁሽሽ ያሉ ሰካራሞች፤ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ ያጡ የነጡ ድሆች!” ይህ ለጆሮ የሚከብድ አስተያየት ነው፤ ቢሆንም ቸንስተኮቫ፣ ፖላንድ ውስጥ በመኖሪያ ቤት እጦት የሚሠቃዩ ሰዎችን ለመርዳት የሚንቀሳቀሱ የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች እንደገለጹት ከሆነ ብዙዎች የአንገት ማስገቢያ የሌላቸውን ሰዎች የሚመለከቷቸው እንደዚህ ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ዚ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሔት እንደዘገበው በኡላንባታር፣ ሞንጎሊያ ካሉት በርካታ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች መካከል አብዛኞቹ መጥፎ ጠረን ባላቸው የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች ያሉበት ሁኔታ በርካታ ሞንጎሊያውያንን ያሳዘነ ቢሆንም የችግሩ መንስኤ “ሰዎች ልጆቻቸውን ለመንከባከብ እጅግ ሰነፎች መሆናቸው ነው” የሚል አስተሳሰብ እንዳላቸው መጽሔቱ ገልጿል።

በሌላ የዓለም ክፍል ደግሞ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች ኅብረተሰቡን ከወንጀል እንታደጋለን በሚሉ ነፍሰ ገዳይ ቡድኖች በመታደን ላይ ይገኛሉ። ለምን? በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታተመ አንድ ጽሑፍ ሁኔታውን እንደሚከተለው ሲል ገልጾታል:- “በላቲን አሜሪካ በፍትሕ ተቋማት፣ በፖሊስ፣ በመገናኛ ብዙኃንና በንግዱ ኅብረተሰብ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ጨምሮ አጠቃላይ ሕዝቡ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆችን የሚመለከታቸው ለሠለጠነው ማኅበረሰብ ስጋት እንደሆኑ አድርጎ ነው።” ከዚህም በላይ “በሪዮ ዲ ጄኔሮ በየቀኑ በአማካይ ሦስት የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች እንደሚገደሉ” ይኸው ምንጭ ተናግሯል።

ቸንስተኮቫ ውስጥ በመኖሪያ ቤት እጦት የሚሠቃዩ ሰዎችን ለመርዳት የሚንቀሳቀሱ የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች በከፈቱት ድረ ገጽ ላይ መኖሪያ ቤት የሌላቸው ሰዎች “ለፍርሃትና ለስጋት ዳርገውናል . . . ይሁንና እነርሱም እንደኛው የረሃብ ስሜት ያላቸው ሰዎች ናቸው። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሲሆኑ ከፍተኛ ችግር አለባቸው።” ይኸው ምንጭ አክሎ “ለችግራቸው የሚደርሱላቸው ሰዎች ይኖራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብሏል። እነዚህ ሰዎች በእርግጥ ችግራቸው ምንድን ነው? ችግሩስ ምን ያህል አሳሳቢ ነው?

[በገጽ 21 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

መኖሪያ ቤት የሌላቸው በርካታ ሕፃናት በዚህ ሰው ሠራሽ ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ

[ምንጭ]

Jacob Ehrbahn/Morgenavisen Jyllands-Posten