በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የእርጅና ዘመን አስደሳች ሊሆን ይችላል?

የእርጅና ዘመን አስደሳች ሊሆን ይችላል?

የእርጅና ዘመን አስደሳች ሊሆን ይችላል?

ቦታው በስዌቶደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው፤ ጊዜው ከጠዋቱ 12:​30 ሲሆን የክረምቱ ብርድ የሚቻል አይደለም። ኤቨለን ከአልጋቸው የሚነሱበት ሰዓት ደርሷል። * ቤቱ ማሞቂያ ስለሌለው ቅዝቃዜው አጥንታቸው ውስጥ ገብቷል።

ከአልጋቸው ጫፍ ላይ ተቀምጠው በአርትራይትስ በሽታ የተጎዳውን ጉልበታቸውን በቀስታ ለማፍታታት ሞከሩ። ከዚያም ብርታት እስኪያገኙ እዚያው ቁጭ ብለው ቆዩ። ቀስ በቀስም እግራቸው ላይ የሚሰማቸው ቁርጥማት ቀነሰ። በዚህ ጊዜ ኤቨለን እንደምንም ራሳቸውን አበረታተው ቀስ ብለው ቆሙ። ይሁን እንጂ ሕመም ስለተሰማቸው አቃሰቱ። ከዚያም እጃቸውን ወገባቸው ላይ አድርገው ‘እንደ አንበጣ ራሳቸውን እየጎተቱ’ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄዱ።​—⁠መክብብ 12:​5 *

ኤቨለን ‘ዛሬስ በርትቻለሁ!’ በማለት ለራሳቸው ተናገሩ። አንድ ተጨማሪ ቀን በሕይወት በመኖራቸው ብቻ ሳይሆን በሕመም የሚያሰቃያቸውን ሰውነት ማንቀሳቀስ በመቻላቸውም ደስ ብሏቸዋል።

ይሁን እንጂ ሌላም የሚያሳስባቸው ነገር አለ። ኤቨለን “አእምሮዬን ሳትኩ እንዴ” አሉ። አልፎ አልፎ ቁልፋቸውን የት እንዳስቀመጡ ይረሳሉ፤ ሆኖም አእምሯቸው አሁንም ንቁ ነው። ኤቨለን “በዕድሜ የገፉ አንዳንድ ሰዎች እንደሚያጋጥማቸው እኔም አእምሮዬን እንዳልስት እጸልያለሁ” በማለት ይናገራሉ።

ኤቨለን በወጣትነት ዕድሜያቸው ስለ እርጅና በጭራሽ አስበው አያውቁም። አሁን ግን ዓመታቱ በድንገት አልፈው በሕመም የሚያሰቃያቸው አካላቸው የ74 ዓመት አዛውንት እንደሆኑ ያስታውሳቸዋል።

አንዳንዶች ከኤቨለን የተሻለ ኑሮ ስላላቸው እንዲሁም በአንጻራዊ ሁኔታ ከባድ የጤና እክልና ጭንቀት ስለሌለባቸው የኋለኞቹ ዓመታት አስደሳች እንደሆኑላቸው ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች እንደ አብርሃም ‘ዕድሜ እንደጠገቡና መልካም የሽምግልና’ ዘመን ላይ እንደደረሱ ያስባሉ። (ዘፍጥረት 25:​8) ሌሎች ደግሞ ‘የጭንቀት ጊዜና ዓመታት’ እንደደረሱባቸውና በሕይወት ‘ደስ እንደማይሰኙ’ ይናገራሉ። (መክብብ 12:​1) አንድ ጥናት እንዳመለከተው በጣም ብዙ ሰዎች በጡረታ ለሚያሳልፏቸው ዓመታት ካላቸው አፍራሽ አመለካከት የተነሳ፣ ኒውስዊክ መጽሔት አስደሳች ዘመን የሚባለው ጊዜ ስሙ ተቀይሮ “የጨለማ ዘመን” መባል አለበት ሲል ዘግቧል።

ለኋለኛው የዕድሜ ዘመን ምን አመለካከት አለህ? አረጋውያን የሚያጋጥሟቸው አንዳንድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? ዕድሜ ሲገፋ አእምሮ እየደከመ መሄዱ የማይቀር ነገር ነው? በዚህ አስደሳች በተባለው የእርጅና ዘመን የአእምሮ ሰላም ለማግኘት ምን ማድረግ ይቻላል?

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

^ አን.2 በዚህ ተከታታይ ርዕስ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

^ አን.3 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በመክብብ መጽሐፍ ላይ የሚገኘው ይህ ጥቅስ የዕድሜ መግፋት የሚያስከትለውን ሥቃይ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ጥሩ አድርጎ እንደሚገልጽ ከታወቀ ቆይቷል።