በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ድንቅ ብሮሹር ነው!”

“ድንቅ ብሮሹር ነው!”

“ድንቅ ብሮሹር ነው!”

በብራዚል የሚኖር አንድ የጂኦግራፊ አስተማሪ የንቁ! መጽሔት ከትምህርት አኳያ ያለውን ጥቅም በተመለከተ አድናቆቱን እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ይህ መጽሔት በትምህርቱ መስክ ከሚቀርቡልን የማስተማሪያ ጽሑፎች በተሻለ መልኩ ለማስተማር የሚረዱ ርዕሶችን ይዞ እንደሚወጣ ተረድቻለሁ። የይሖዋ ምሥክር ባልሆንም እንኳ ንቁ! መጽሔት ጠቃሚ መሆኑን ከልብ አምናለሁ።”

ያም ሆኖ፣ ይህ አስተማሪ የንቁ! መጽሔት የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያዘጋጇቸው ብዙ ጽሑፎች መካከል አንዱ ብቻ እንደሆነ ተገንዝቧል። እንዲህ በማለት ጽፏል:- “አንድ የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ’ (እንግሊዝኛ) የተባለውን ብሮሹር አዋሰኝ። ብሮሹሩ በያዘው ጥራት ያለው መረጃ በጣም ተደንቄያለሁ። ድንቅ ብሮሹር ነው! በተለይ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑ ታሪኩን በዓይነ ሕሊናቸው መሳላቸውና የት አካባቢ እንደተፈጸመ ማወቃቸው ጥናቱን ይበልጥ ትርጉም ያለው ያደርግላቸዋል።”

“ጽሑፎቻችሁን ሁሉም ቦታ ማግኘት ይቻላል። ለምሳሌ በአውቶቡስ ውስጥ፣ ተማሪዎች ጋር ሌላው ቀርቶ ባንክ ቤት ወረፋ በሚጠበቅበት ቦታ ላይ እንኳ ይኖራሉ። ጽሑፎቻችሁ በቂ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነባቸው ቦታዎች እንኳ ሳይቀር መድረሳቸው አስደስቶኛል። ስለ ግሩም ሥራችሁ ልትመሰገኑ ይገባችኋል” በማለት አክሎ ተናግሯል።

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለው ብሮሹር በ80 ቋንቋዎች ይገኛል። ብሮሹሩ ባለ ቀለም ካርታዎችና ፎቶግራፎች ያሉት ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረውን ዓለም በተለይ ደግሞ ተስፋይቱ ምድር በተለያየ ጊዜ የነበራትን ገጽታ በግልጽ ያስቀምጣል። ይህን ባለ 36 ገጽ ብሮሹር ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

የብሮሹሮቹ ሽፋን:- Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.