በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

እንዲህ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሞተበት ዕለት ነው። ለኢየሱስ ሞት ትልቅ ግምት የተሰጠው ለምንድን ነው? በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ ነው።

ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ መሆኑ ሰዎች ለአምላክ ያላቸውን ታማኝነት ይዘው መቀጠል እንደሚችሉ አረጋግጧል።

በተጨማሪም የክርስቶስ ሞት ከሰው ልጆች መካከል የተወሰኑት ከእርሱ ጋር በሰማይ የመግዛት አጋጣሚ እንዲያገኙ አስችሏል። እንዲሁም ብዙዎች ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ከፍቷል።

ኢየሱስ በፍቅር በመነሳሳት መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበውን ሥጋና ደሙን ለማመልከት በሞቱ ዋዜማ ምሽት ላይ ያልቦካ ቂጣና ቀይ የወይን ጠጅ ተጠቀመ። ደቀ መዛሙርቱንም “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው። (ሉቃስ 22:​19) አንተስ ይህን ታላቅ ክንውን አስበህ ትውላለህ?

የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ በዓል ሲያከብሩ አብረሃቸው እንድትገኝ በአክብሮት ይጋብዙሃል። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው ረቡዕ ሚያዝያ 12, 2006 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 4, 1998 ) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። ለቤትህ ቅርብ በሆነው የመንግሥት አዳራሽ ተገኝተህ በዓሉን ማክበር ትችላለህ። በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክህ በአቅራቢያህ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር።