በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልጆቻችንን ከችግር ለመጠበቅ የተዘጋጀ እርዳታ

ልጆቻችንን ከችግር ለመጠበቅ የተዘጋጀ እርዳታ

ልጆቻችንን ከችግር ለመጠበቅ የተዘጋጀ እርዳታ

ባለፈው ዓመት በቨርጂንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አንዲት ሴት ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ (መጽሐፉ በአማርኛ አልተተረጎመም) ስለተባለው መጽሐፍ እንዲህ ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል:- “የ4፣ የ6 እና የ7 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የልጅ ልጆቼ ከመተኛታቸው በፊት ‘እማማ፣ ስለ ኢየሱስ ከሚናገረው መጽሐፍ አንድ ታሪክ አንብቢልን’ ይሉኛል፤ ታሪኮቹንም እጅግ ወደዋቸዋል።”

እኚህ አያት እንዲህ ሲሉ አክለው ተናግረዋል:- “በምዕራፍ 32 ላይ የሚገኘውን ‘ኢየሱስ ጥበቃ ያገኘው እንዴት ነው?’ የሚለውን ርዕስ አንብቤዋለሁ። ርዕሰ ትምህርቱ ይሖዋ ለኢየሱስ እንዴት ጥበቃ እንዳደረገለት ከገለጸ በኋላ፣ ልጆች ራሳቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ የሚረዳ ተግባራዊ ምክር መለገሱ እጅግ አስደንቆኛል። ጽሑፉ እንዲህ ይላል:- ‘አንድ ሰው እንዲህ ለማድረግ ከሞከረ ጠበቅ አድርገህ “ተው! እናገርብሃለሁ!” በማለት ድምፅህን ከፍ አድርገህ ተናገር።’”

ቤትሳይዳ የተባለች የአምስት ዓመት ሴት ልጅ ያለቻት በሜክሲኮ የምትኖር አንዲት እናት ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ከልጅዋ ጋር አንብባ መጨረሷን ተናግራለች። ይህቺ እናት እንዲህ ብላለች:- “ዓለም በሥነ ምግባር የባሰ እያዘቀጠ ሄዷል፤ ልጆቻችንም ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ጫና ይደረግባቸዋል። ልጄ፣ በምዕራፍ 32 ላይ የሰፈሩትን የመሰሉ ራሷን ተገቢ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች እንዴት መጠበቅ እንዳለባት የሚገልጹ መመሪያዎች በማግኘቷ አመስጋኝ እንደሆነች ተናግራለች።”

ይህ ውብ ስዕሎችን የያዘውና ከዚህ መጽሔት ጋር ተመሳሳይ መጠን ያለው ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ መሠረት ማሠልጠን እንዲችሉ ይረዳቸዋል። (ምሳሌ 22:6) የኢየሱስን ትምህርቶች መሠረት በማድረግ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ በቀላል ቋንቋ የቀረበ ቢሆንም በውስጡ የሰፈሩት ቁም ነገሮች በየትኛውም ዕድሜ ለሚገኙ ሰዎች ጠቃሚ ናቸው። ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።