በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ማንበቤን ማቆም አልቻልኩም”

“ማንበቤን ማቆም አልቻልኩም”

“ማንበቤን ማቆም አልቻልኩም”

▪ ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ በተደረጉት የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ትምህርቶች ለማጥናት የሚረዳ ውብ ሥዕሎችን ያካተተ ባለ 224 ገጽ አዲስ መጽሐፍ ወጥቶ ነበር። የመጽሐፉ ርዕስ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ነው።

አንዲት አንባቢ “ማንበቤን ማቆም አልቻልኩም” ስትል ጽፋለች። አክላም “ይህ መጽሐፍ ባሉት ጥቂት ገጾች ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ያነበብኳቸው የማጥኛ መጽሐፎች በጠቅላላ የያዟቸው በጣም ጠቃሚ ጎኖች ሁሉ ተካትተዋል” ብላለች።

ሌላ አንባቢ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:- “እያንዳንዱ ገጽ ማንበባችሁን እንድትቀጥሉ ይገፋፋችኋል። ከዚህም በላይ በየምዕራፉ መደምደሚያ ላይ የሰፈሩት ሐሳቦች የሚቀጥለው ምዕራፍ ምን እንደሚዳስስ የሚጠቁሙበት መንገድ በጣም አስደስቶኛል። መጽሐፉ ዓይኖቼ እንባ እስኪያቀሩ ድረስ የነኩኝ ብዙ ክፍሎች አሉት። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የወደድኳቸው በርካታ ነገሮች አሉ፤ እነዚህን ገጽታዎች ሁሉ ብጽፍ አንድ መጽሐፍ ይወጣቸዋል!”

ሌላም ሰው አድናቆታቸውን እንዲህ ብለው ጽፈዋል:- “እውነቴን ነው የምላችሁ፣ ይህ መጽሐፍ በዋጋ ሊተመን የማይችል ውድ የሆነ መንፈሳዊ ሀብት ነው፤ አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር እርዳታ የሚያበረክት ግሩም መሣሪያ ይሆነናል።”

ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ በቀረበው ጥያቄ መሠረት በአሁኑ ጊዜ 140 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።