በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ይህ የሆነው የት ነበር?

1. ይህ ድርጊት የተፈጸመው የት ከተማ ነው?

መልስህን በካርታው ላይ አክብብ።

ጠርሴስ

አንጾኪያ (ሶርያ ውስጥ የምትገኘው)

ደማስቆ

ኢየሩሳሌም

◆ ቅርጫቱ ውስጥ ያለው ማን ነው?

......

◆ ከከተማው የሚሸሸው ለምንድን ነው?

......

▪ ለውይይት:- ከችግር መሸሽ ያለብህ መቼ ነው? ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ከችግር መሸሽ ይኖርባቸዋል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ዘመኑ መቼ ነበር?

ሥዕሉንና ታሪኩ የተፈጸመበትን ትክክለኛ ዘመን በመሥመር አገናኝ።

1513 ከክ.ል. በፊት 1512 1473 1450 468 455

2. ኢያሱ 24:1-25

3. ዘፀአት 32:1-6, 19

4. ዕዝራ 8:1, 21, 31

እኔ ማን ነኝ?

5. ልብስ ሰፊ ነበርኩ፤ ሁለቱም ስሞቼ “የሜዳ ፍየል” የሚል ትርጉም ያላቸው ሲሆን ከሞት ተነስቼ ነበር።

እኔ ማን ነኝ?

6. የምኖረው በባሕር አጠገብ ሲሆን በአንድ ወቅት ዓሣ ማጥመድ የሚወድ ታዋቂ የሆነ እንግዳ እኔ ጋር አርፎ ነበር። ሞክሼዎችም ነን።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 8 አንድ ባል ሚስቱን መያዝ ያለበት እንዴት ነው? (ቈላስይስ 3:․․․)

ገጽ 8 በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት የሚቻልበት በጣም ጥሩ የሆነው መንገድ ምንድን ነው? (1 ጴጥሮስ 4:․․․)

ገጽ 15 አምላክ የሚኖረው በአንድ የተወሰነ ቦታ ነው? (1 ነገሥት 8:․․․)

ገጽ 25 በሥራ ምርጫ ረገድ ከሁሉ የተሻለ ምክር ማግኘት የምትችለው ከየት ነው? (ምሳሌ 3:․․․)

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

(መልሶቹ በገጽ 13 ላይ ይገኛሉ)

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ደማስቆ።—የሐዋርያት ሥራ 9:19, 25

◆ በኋላ ጳውሎስ የተባለው ሳውል።—የሐዋርያት ሥራ 9:17-19

◆ በመስበኩ ምክንያት አይሁዳውያን ሊገድሉት ይፈልጉ ስለነበር ነው።—የሐዋርያት ሥራ 9:22-24

2. 1450 ከክርስቶስ ልደት በፊት

3. 1513 ከክርስቶስ ልደት በፊት

4. 468 ከክርስቶስ ልደት በፊት

5. ጣቢታ ወይም ዶርቃ።—የሐዋርያት ሥራ 9:36-41

6. ቁርበት ፋቂው ስምዖን።—የሐዋርያት ሥራ 10:5, 6