በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

በዚህ ሥዕል ላይ ምን ስህተት ይታይሃል?

በዘፍጥረት 3:1-5 ላይ ከሚገኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ጋር የማይስማሙትን ሦስት ነገሮች ለይተህ ጻፍ።

1. ......

2. ......

3. ......

▪ ለውይይት:- ይሖዋ፣ አዳምንና ሔዋንን መልካምና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ እንዳይበሉ የከለከላቸው ለምን ነበር? የይሖዋን መመሪያዎች መታዘዝ አስፈላጊ የሆነው ለምን ይመስልሃል?

ዘመኑ መቼ ነበር?

ከታች ያሉትን ሥዕሎች ከተፈጠሩበት “ቀን” ጋር በመስመር አገናኝ።

1ኛ ቀን 2ኛ ቀን 3ኛ ቀን 4ኛ ቀን 5ኛ ቀን 6ኛ ቀን 7ኛ ቀን

4. ዘፍጥረት 1:14-16

5. ዘፍጥረት 1:24

6. ዘፍጥረት 1:20, 21

እኔ ማን ነኝ?

7. ከተማ በመቆርቆር በጽሑፍ የሰፈርኩት የመጀመሪያው ሰው ነኝ።

እኔ ማን ነኝ?

8. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሔዋን ቀጥሎ ስሜ የተጠቀሰው የመጀመሪያዋ ሴት ነኝ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 5 በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ግድግዳ ላይ በመውጣት ችሎታዋ የታወቀችው እንስሳ ማን ትባላለች? (ምሳሌ 30:․․․ NW)

ገጽ 9 ይሖዋ ሊወደስ የሚገባው ለምንድን ነው? (ራእይ 4:․․․)

ገጽ 20 በዘፍጥረት ዘገባ ላይ የሚገኘው ጥልቅ እውቀት የምን ማስረጃ ነው? (2 ጢሞቴዎስ 3:․․․)

ገጽ 25 አምላክ ሁሉንም ነገር “በጊዜው” እንዴት አድርጎ ነው የሠራው? (መክብብ 3:․․․)

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

(መልሱ በገጽ 12 ላይ ይገኛል)

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. እባቡ ያናገረው ሔዋንን እንጂ አዳምን አይደለም።—ዘፍጥረት 3:1

2. አዳምና ሔዋን ልጆች የወለዱት ከኤድን ገነት ከተባረሩ በኋላ ነበር።—ዘፍጥረት 4:1

3. አዳምና ሔዋን በኤድን ገነት ሲኖሩ ዕራቁታቸውን ነበሩ።—ዘፍጥረት 2:25

4. አራተኛ “ቀን።”—ዘፍጥረት 1:14-16, 19

5. ስድስተኛ “ቀን።”—ዘፍጥረት 1:24, 31

6. አምስተኛ “ቀን።”—ዘፍጥረት 1:20, 21, 23

7. ቃየን።—ዘፍጥረት 4:17

8. ዓዳ።—ዘፍጥረት 4:19

[በገጽ  31 ላይ የሚገኙ የሥዕል ምንጮች]

የመጀመሪያው ክብ:- Breck P. Kent; ሁለተኛው ክብ:- © Pat Canova/Index Stock Imagery