በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ችግር ያጋጠማትን አንዲት ወጣት ረዳት

ችግር ያጋጠማትን አንዲት ወጣት ረዳት

ችግር ያጋጠማትን አንዲት ወጣት ረዳት

በሜክሲኮ የምትኖር ሲቢያ የተባለች የ13 ዓመት ተማሪ አንዲት የክፍል ጓደኛዋ አብዛኛውን ጊዜ እያለቀሰች ወደ ትምህርት ቤት እንደምትመጣ አስተዋለች። ሲቢያ ልጅቷን ልታጽናናት ትሞክር ነበር። አንድ ቀን ይህች ልጅ አባቷ የአልኮል ሱሰኛ እንደሆነና እናቷን በተደጋጋሚ እንደሚደበድባት ለሲቢያ ነገረቻት።

ሲቢያ እንዲህ ትላለች:- “የክፍል ጓደኛዬ መኖር እንደማትፈልግና ራሷን ለማጥፋት ሙከራ እስከማድረግ ደርሳ እንደነበር እንዲሁም ማንም እንደማይወዳትና በዚህ ምክንያት ብቸኝነት እንደሚሰማት አጫወተችኝ። እኔም በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያለው ከሁሉ የላቀ አካል በጣም እንደሚወዳት ነገርኳት። ከዚያም ይሖዋ ለሰው ዘር ያለውን ዓላማ ገለጽኩላት።”

በኋላም ሲቢያ ለክፍል ጓደኛዋ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተሰኘውን መጽሐፍ ሰጠቻትና በእረፍት ሰዓት መጽሐፉን ማጥናት ጀመሩ። ልጅቷም ቀስ በቀስ ራሷን ማግለሏን በመተው ከሌሎች ጋር መሳቅ መጫወት ጀመረች። ለሲቢያ የጻፈችላት ደብዳቤ እንዲህ ይላል:- “ጓደኛዬ ስለሆንሽና ችግሬን ስለተረዳሽልኝ አመሰግንሻለሁ። ሁልጊዜ እንደ አንቺ ዓይነት እህት እንዲኖረኝ እመኝ ነበር። አሁን ይሖዋ እንደሚያስብልኝ አውቄያለሁ።”

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ከተባለው መጽሐፍ ሊጠቀም የሚችል አንድ ወጣት ያውቁ ይሆናል። ይህ መጽሐፍ ከያዛቸው 39 ምዕራፎች ውስጥ “እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?”፣ “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?” እና “እውነተኛ ፍቅር መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?” የሚሉት ርዕሶች ይገኙበታል። የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።