አምላክ ያስብልናል!
አምላክ ያስብልናል!
አምላክ በኤደን የተጀመረውን ዓመጽ የያዘበት መንገድ ለእያንዳንዳችን ያለውን ጥልቅ ፍቅርና ስለ ወደፊቱ ሕይወታችን እንደሚያስብ የሚያሳይ ነው። አምላክ በእርግጥ እንደሚያስብልን የሚያረጋግጠውን የሚከተለውን ማስረጃ ተመልከት። እንዲሁም ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱትን ጥቅሶች ከራስህ መጽሐፍ ቅዱስ እያወጣህ አንብባቸው።
● ምድርን ማራኪ የሆነ ተፈጥሯዊ ውበት አላብሶ፣ አስደናቂ በሆኑ እንስሳት የተሞላችና ለም አድርጎ ሰጥቶናል።—የሐዋርያት ሥራ 14:17፤ ሮሜ 1:20
● አምላክ በዕለት ተዕለት በሚያጋጥሙን ነገሮች እንድንደሰት አስደናቂ አካል ሰጥቶናል። ለምሳሌ፣ ጥሩ ምግቦች በማጣጣም፣ ፀሐይ ስትጠልቅ በማየት ደስታ እናገኛለን፤ እንዲሁም የሕፃን ልጅ ሳቅ ስንሰማ ብሎም የምንወዳቸው ሰዎች በፍቅር ስሜት ሲዳብሱን እንደሰታለን።—መዝሙር 139:14
● የሚያጋጥሙንን አንዳንድ ችግሮችና ተጽዕኖዎች መቋቋም እንድንችል ጥበብ ያለበት መመሪያ አዘጋጅቶልናል።—መዝሙር 19:7, 8፤ 119:105፤ ኢሳይያስ 48:17, 18
● ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም መኖርንና በሞት የተለዩን የምንወዳቸው ሰዎች ሲነሱ ማየትን ጨምሮ አስደሳች ተስፋዎችን ሰጥቶናል።—ሉቃስ 23:43፤ ዮሐንስ 5:28, 29
● ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዲኖረን ለማስቻል ለእኛ ሲል እንዲሞት አንድያ ልጁን ወደ ምድር ልኮታል።—ዮሐንስ 3:16
● መሲሐዊ መንግሥት በሰማይ አቋቁሟል፣ እንዲሁም መንግሥቱ በቅርቡ ምድርን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደሚጀምር የሚጠቁሙ በርካታ ማስረጃዎችን ሰጥቶናል።—ኢሳይያስ 9:6, 7፤ ማቴዎስ 24:3, 4, 7፤ ራእይ 11:15፤ 12:10
● በጸሎት ወደ እርሱ እንድንቀርብና ልባችንን እንድናፈስለት ጋብዞናል፤ እንዲህ ካደረግን ደግሞ በእርግጥ ይሰማናል።—መዝሙር 62:8፤ 1 ዮሐንስ 5:14, 15
● ሰዎችን እንደሚወዳቸውና እንደሚያስብላቸው በተደጋጋሚ ጊዜያት አረጋግጦላቸዋል።—1 ዮሐንስ 4:9, 10, 19