በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ ስጦታ

ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ ስጦታ

ከፍተኛ አድናቆት ያተረፈ ስጦታ

አንድ ስጦታ፣ ተቀባዩ የሚያስፈልገውን ነገር ሲያሟላና አድናቆት ሲያተርፍ ሰጪውም ሆነ ተቀባዩ ይደሰታሉ። በቅርብ ጊዜ በሜክሲኮ የሚኖሩ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው አንዲት የመንግሥት ሠራተኛ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ (በአማርኛ አልተተረጎመም) የተባለውን መጽሐፍ በማግኘታቸው ለይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ምስጋናቸውን ገልጸዋል። ደብዳቤያቸው በከፊል እንዲህ ይላል:-

“በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው ትምህርት በጣም ጠቃሚ ነው። ሐሳቡ የተወሰደው በጣም ጥንታዊ ከሆነ መጽሐፍ ቢሆንም ትምህርቱ ወቅታዊና ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚጠቅም መሆኑን ተገንዝቤያለሁ።

“ወላጅ እንደመሆናችን መጠን ልጆቻችን ምን ዓይነት ባሕርይ ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲያስተውሉ የሚረዷቸውንና ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያግዟቸውን እንዲሁም በዓለም ላይ የሌለውን አክብሮትና ታማኝነት ለማዳበር የሚያስችሏቸውን የሥነ ምግባር እሴቶች በውስጣቸው መቅረጽ እንዳለብን አምኛለሁ። ከሁሉም በላይ ደግሞ አፍቃሪና ደግ የሆነ እንዲሁም ከፍተኛ ኃይል ያለው አካል መኖሩን እንዲገነዘቡ መርዳት አለብን። የላካችሁልኝ መጽሐፍ፣ ፈጣሪያችን ለወላጆች የሰጠውን ልጆቻችን ጎረቤቶቻቸውን የሚወዱ ሰዎች እንዲሆኑ አድርጎ የማሳደግ ኃላፊነት በመወጣት ረገድም ሆነ በተሠማራሁበት የሙያ መስክ በእጅጉ ይጠቅመኛል ብዬ አምናለሁ።”

እኚህ ሴት ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ በተባለው መጽሐፍ ላይ ከሰፈሩት የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶችና ምሳሌዎች ጠቃሚ ትምህርት ሊገኝ እንደሚችል ተገንዝበዋል። እርስዎም ውብ የሆኑ ሥዕሎችን ያካተተውን ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት ይችላሉ። ይህንን መጽሐፍ ለማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።