በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“የሴት አያቶችን ቀን ታከብሪያለሽ?”

“የሴት አያቶችን ቀን ታከብሪያለሽ?”

“የሴት አያቶችን ቀን ታከብሪያለሽ?”

ወቅቱ ብርዳማ ክረምት ነበር፤ በፖላንድ የምትኖር ናታሊያ የተባለች የ16 ዓመት ወጣት አንድ ቀን ጠዋት ባቡር እየጠበቀች ሳለ ሁለት ጋዜጠኞች ወደ እርሷ ጠጋ ብለው “የሴት አያቶችን ቀን ታከብሪያለሽ?” ሲሉ ጠየቋት።

በፖላንድ አገር የሴት አያቶች ቀን፣ የወንድ አያቶች ቀን፣ የእናቶች ቀን፣ የሴቶች ቀንና የአስተማሪዎች ቀን የሚባሉት ቀናት በሙሉ ልዩ ግምት ይሰጣቸዋል። ትንንሽ ልጆች የሴት አያቶችን ቀንም ሆነ የወንድ አያቶችን ቀን በአብዛኛው የሚያከብሩት የመልካም ምኞት መግለጫ ካርዶችን በማዘጋጀት ሲሆን ከፍ ከፍ ያሉት ልጆች ደግሞ ለአያቶቻቸው ስጦታ ወይም አበባ በመስጠት ነው።

ናታሊያ መጀመሪያ ላይ ጥያቄው ሲቀርብላት የምትለው ጠፍቷት ነበር። ይሁንና በልቧ ከጸለየች በኋላ ጋዜጠኞቹን “የይሖዋ ምሥክር ስለሆንኩ የሴት አያቶችን ቀን አላከብርም” አለቻቸው። ጋዜጠኞቹ ያልጠበቁት ነገር ሆነባቸው። በዚህ ጊዜ ናታሊያ ፈገግ ብላ “የምኖረው ከሴት አያቴ ጋር ነው። በመሆኑም በየቀኑ አበባ ልሰጣት፣ ላጫውታትና ስለ ደግነቷ ላመሰግናት እችላለሁ። ታዲያ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ክብር የምሰጣት ለምንድን ነው?” አለቻቸው።

ይህ ማስተዋል የታከለበት መልስ አንተንም ሊያስደንቅህ እንደሚችል ሁሉ ጋዜጠኞቹንም አስገርሟቸዋል። በማግስቱ ጠዋት አንድ ጋዜጣ ናታሊያ የተናገረችውን ሐሳብና ፎቶግራፏን ይዞ ወጣ።

የናታሊያ ምሳሌ ‘እኔስ እምነቴንና አኗኗሬን በተመለከተ በድንገት ጥያቄ ቢቀርብልኝ ማብራሪያ ለመስጠት ምንጊዜም ዝግጁ ነኝ?’ ብለህ ራስህን እንድትጠይቅ አላነሳሳህም? የአምላክ እውነተኛ አገልጋዮች ስለ እምነታቸው በምክንያት ለማስረዳት ሁልጊዜ ዝግጁ በመሆንና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመመሥከር ንቁ በመሆን እርሱን ለማክበር ይጥራሉ።—1 ጴጥሮስ 3:15