ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን መጽናኛ
ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን መጽናኛ
▪ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለው 32 ገጾች ያሉት ባለ ሙሉ ቀለም ብሮሹር እንዲህ የመሰለውን መጽናኛ ይሰጣል። ይህ ብሮሹር የሚወዱትን ግለሰብ በሞት በማጣታቸው ምክንያት ያዘኑ ሰዎች ስለሚያጋጥሟቸው አሉታዊ ስሜቶች ግንዛቤ እንዲያገኙና እነዚህንም ስሜቶች መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ብሮሹሩ ሐዘን የደረሰባቸውን ሰዎች እንዴት ማጽናናት እንደሚቻል የሚያብራራ ክፍል አለው።
ይህ ብሮሹር ‘ከሐዘኔ ልጽናና የምችለው እንዴት ነው? የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?’ እንደሚሉት ላሉ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። በተጨማሪም ስለ ሞትና ሙታን ስላሉበት ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ማብራሪያ ይዟል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ስለሰጠው በጸዳች ምድር ላይ በገነት ውስጥ ስለሚገኘው የትንሣኤ ተስፋ ጎላ አድርጎ ይገልጻል።
እርስዎ ወይም አንድ የሚያውቁት ሰው ይህን ብሮሹር በማንበብ መጽናኛ ማግኘት ትችሉ ይሆናል። ብሮሹሩን ማግኘት ከፈለጉ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ።
ይህን ብሮሹር ለማዘዝ ቅጹን ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ የምትወዱት ሰው ሲሞት የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።