በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ምሳሌውን አብራራ

1. በማቴዎስ 18:23-35 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ አገልጋዩ ንጉሡን የለመነው ምን እንዲያደርግለት ነው?

․․․․․․

2. የመጀመሪያው አገልጋይ ባልንጀራው የሆነውን ሌላኛውን አገልጋይ ምን አደረገው?

․․․․․․

3. ንጉሡ በመጀመሪያው አገልጋይ ላይ የተቆጣው ለምንድን ነው?

․․․․․․

ለውይይት:- በቅርቡ ለአንድ ግለሰብ ይቅርታ ያደረግኸው መቼ ነው? ምን ስላደረገህ ነው የተናደድከው? ይቅር ያልከውስ ለምንድን ነው?

ዘመኑ መቼ ነበር?

ከታች የተዘረዘሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የጻፉት እነማን እንደሆኑ በጽሑፍ አስፍር። እንዲሁም መጻሕፍቱን ተጽፈው ካለቁበት ዘመን ጋር በመስመር አገናኝ።

1657 ከክ.ል.በፊት

1513 ከክ.ል.በፊት 1100 ከክ.ል.በፊት ገደማ 56 ከክ.ል.በኋላ ገደማ 61 ከክ.ል.በኋላ ገደማ

4. ዘፍጥረት

5. መሳፍንት

6. የሐዋርያት ሥራ

እኔ ማን ነኝ?

7. ሁለቱ መንታ ልጆቼ ሁለት ብሔራት ሆነዋል።

እኔ ማን ነኝ?

8. ሐዋርያ እንድሆን ዕጣ አልወጣልኝም።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 3 በቅርቡ የሚወገዱት የጤና እክሎች የትኞቹ ናቸው? (ኢሳይያስ 35:․․․)

ገጽ 11 ዘላቂ ጤንነት ማግኘት ይቻላል የሚል እምነት ልታሳድር የቻልከው ለምንድን ነው? (ሉቃስ 18:․․․)

ገጽ 20 የኖኅ መርከብ ቁመቷ፣ ርዝመቷና ስፋቷ ምን ያህል ነበር? (ዘፍጥረት 6:․․․)

ገጽ 30 ትዳር ለመመሥረት ከማሰብህ በፊት ከምን ዓይነት ድርጊቶች መራቅና የትኞቹን ባሕርያት መኮትኮት ይገባሃል? (ኤፌሶን 4:․․․)

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

(መልሱ በገጽ 26 ላይ ይገኛል)

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ዕዳውን ይቅር በማለት ምሕረት እንዲያሳየው።

2. ወደ እስር ቤት አስገባው።

3. አገልጋዩ ምሕረት ስላላሳየ።

4. ሙሴ፣ በ1513 ከክ. ል. በፊት

5. ሳሙኤል፣ በ1100 ከክ. ል. በፊት ገደማ

6. ሉቃስ፣ በ61 ከክ. ል. በኋላ ገደማ

7. ርብቃ።—ዘፍጥረት 25:21-23

8. በርስያን።—የሐዋርያት ሥራ 1:23-26

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

የመሃለኛው ክብ ምስል:- Scott Bauer/​Agricultural Research Service, USDA