በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አብያተ ክርስቲያናት ወዴት እያመሩ ነው?

አብያተ ክርስቲያናት ወዴት እያመሩ ነው?

አብያተ ክርስቲያናት ወዴት እያመሩ ነው?

አብያተ ክርስቲያናት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? አንተ በምትኖርበት አካባቢ አብያተ ክርስቲያናት ውድቀት እያጋጠማቸው ነው ወይስ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? እንደ አፍሪካ፣ ምሥራቅ አውሮፓና ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ አካባቢዎች ሰዎች ለሃይማኖት ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖታዊ ቡድኖች መጠናቸው እያደገ መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ሰምተህ ይሆናል። ሆኖም ከሌሎቹ የዓለም ክፍሎች፣ በተለይም ከምዕራብ አውሮፓ የሚመጡ የዜና ዘገባዎች እንደሚገልጹት አብያተ ክርስቲያናት እየተዘጉ፣ የተሰብሳቢዎቻቸውም ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየተመናመነ እንዲሁም ሰዎች ለሃይማኖት ያላቸው ፍላጎት እየቀነሰ መጥቷል።

የተሰብሳቢዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መሄዱ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት አሠራራቸውን እንዲቀይሩ አድርጓቸዋል። አንዳንዶቹ አምላክ ማንኛውንም ዓይነት አኗኗር ይቀበላል ብለው በማሰብ በሌሎች ላይ የመፍረድ መብት እንደሌላቸው ይናገራሉ። አብያተ ክርስቲያናት የአምላክን ቃል ከማስተማር ይልቅ ሰዎችን የሚያዝናኑ፣ የሚያስደስቱና የሚስቡ ነገሮችን ወደማድረግ አዘንብለዋል። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ተሳላሚዎች አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለውን ለውጥ ያደረጉት ከዘመናዊው ዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ለመስማማት እንደሆነ ቢሰማቸውም ቅን ልብ ያላቸው በርካታ ሰዎች ግን ኢየሱስ ከሰጠው ተልእኮ እየራቁ መሆናቸው ያሳስባቸዋል። አብያተ ክርስቲያናት ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ ምን ዓይነት ጎዳና እየተከተሉ እንዳሉ እንመልከት።