በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጾታ ግንኙነት ለመታቀብ ስለመወሰን ምን ለማለት ይቻላል?

ከጾታ ግንኙነት ለመታቀብ ስለመወሰን ምን ለማለት ይቻላል?

ከጾታ ግንኙነት ለመታቀብ ስለመወሰን ምን ለማለት ይቻላል?

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በወጣቶች ዘንድ “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት አላደርግም” እንደሚሉት ያሉ በድንግልና የመቆየት ወይም የመታቀብ ቃለ መሐላዎችን መስማት እየተለመደ መጥቷል። እነዚህ ቃለ መሐላዎች ወጣቶች የሚያስመሰግን ዓላማ እንዳላቸው የሚጠቁሙ ከመሆናቸውም ሌላ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛትም ጋር የሚስማሙ ናቸው። (1 ቆሮንቶስ 6:18፤ ኤፌሶን 5:5) ይሁን እንጂ መሐላዎቹ ተፈጻሚነት የማግኘታቸው ጉዳይ አጠያያቂ ነው። አንድ ጥናት እንዳመለከተው ወደ 60 በመቶ የሚጠጉ ወጣቶች የገቡትን ቃል በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አፍርሰዋል።

ከዚህም በላይ አንዳንድ ወጣቶች “መታቀብ” ወይም “ድንግልና” የሚሉትን ቃላት የሚፈቱበት መንገድ አሳሳቢ ነው። ሻርሊን ጃኔቲ እና ማርጋሬት ሳጋራዜ ቦይ ክሬዚ! በተባለው መጽሐፋቸው ላይ የሚከተለውን ጽፈዋል:- “ባለሙያዎች፣ በአፍ ሌላው ቀርቶ በፊንጢጣ የሚፈጸመው የጾታ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ድንግል ሆነው ለመቀጠል ከሚፈልጉ ልጆች ጋር ያያይዙታል። በቀጥታ የጾታ ግንኙነት እስካልፈጸሙ ድረስ ሌላውን ድርጊት ሁሉ እንደ ጾታ ግንኙነት እንደማይቆጥሩት ይናገራሉ።”

ይህ አስተሳሰብ እየተስፋፋ የመጣ ይመስላል። አንድ ደራሲ በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች ቃለ ምልልስ ካደረጉ በኋላ “በአፍ የሚደረገው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በእርግጥ የጾታ ግንኙነት እንደሆነ የሚሰማቸው ምናልባት ከመቶ አንድ ወይም ሁለት ቢሆኑ ነው” ብለዋል። አክለውም “በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወይም ከዚያ የሚያንስ ዕድሜ ያለው ልጃችሁ እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ሊኖረው እንደሚችል መገንዘብ ይኖርባችኋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የመጽሐፍ ቅዱስን የአቋም ደረጃዎች በጥብቅ የሚከተሉ ሁሉ በአፍም ሆነ በፊንጢጣ የሚፈጸመው የጾታ ግንኙነት ስሙም ራሱ እንደሚጠቁመው የጾታ ግንኙነት እንደሆነ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ‘ከዝሙት እንድንርቅ’ (‘ከጾታ ብልግና ሙሉ በሙሉ እንድንቆጠብ፣’ ቱዴይስ ኢንግሊሽ ቨርሽን) የሚሰጠው ትእዛዝ ማንኛውንም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ የጾታ ግንኙነት ያጠቃልላል።—1 ተሰሎንቄ 4:3