በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሊያመልጥዎ የማይገባ በዓል

ሊያመልጥዎ የማይገባ በዓል

ሊያመልጥዎ የማይገባ በዓል

“ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት።” ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሉቃስ 22:19 ላይ የሚገኙትን እነዚህን ቃላት የተናገረው የሞቱን መታሰቢያ በዓል ባቋቋመበት ወቅት ነበር። የሰው ዘሮች በገነት ውስጥ ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዲኖራቸው ያስቻለው የኢየሱስ ሞት ነው። ስለዚህ የእርሱን ሞት መታሰቢያ ማክበራችን የተገባ ነው።

በዚህ ዓመት በሚከበረው የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ላይ ይገኛሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች በጣም አስፈላጊ የሆነውን የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ሲያከብሩ እርስዎም እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ ያቀርቡልዎታል። ይህ ዓመታዊ በዓል በመጽሐፍ ቅዱስ የጨረቃ ቀን አቆጣጠር መሠረት ኒሳን 14 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይከበራል። በዚህ ዓመት በዓሉ ሰኞ መጋቢት 24, 1999 (ሚያዝያ 2, 2007) ላይ ይውላል። በአካባቢዎ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ይህ በዓል እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ የሚከበርበትን ትክክለኛ ቦታና ሰዓት ይነግሩዎታል።