በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

የወጣቶች ጥያቄ . . . ማንበብ ያለብኝ ለምንድን ነው? (ግንቦት 2006) ዕድሜዬ 15 ሲሆን ይህ ጽሑፍ በጣም ጠቅሞኛል። መጽሔቱን ትምህርት ቤት ይዤው ሄጄ ስለነበር አስተማሪዬ ተመለከተችው። በትምህርት ክፍለ ጊዜ አስተማሪያችን የንባብ ልማድ ማዳበር ጥሩ መሆኑን ከተናገረች በኋላ ይህን ንቁ! መጽሔት ለክፍል ጓደኞቼ አሳየቻቸው። በጽሑፉ በጣም እንደተደሰተች የገለጸች ሲሆን ሁሉም እንዲያነቡት ሐሳብ አቀረበች።

ዲ.ኤ.ኬ.፣ ብራዚል

ከዚህ በፊት በመጽሔቱ ላይ ከሚወጡት ርዕሶች መካከል ብዙውን ጊዜ የማነበው የሚስበኝን ብቻ ነበር። አሁን ግን በመጀመሪያ ሳየው የማይስበኝ ቢሆንም እንኳ እያንዳንዱን ርዕስ ለማንበብ ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ። ሁልጊዜ ለማለት ይቻላል መጀመሪያ ላይ የማይስቡኝን ርዕሶች ካነበብኳቸው በኋላ እወዳቸዋለሁ። በጣም አመሰግናችኋለሁ።

ኢ. ጂ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

በዛሬው ጊዜ፣ በአንድ ወቅት እኔ በነበርኩበት ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉ ወጣቶች መኖራቸውን ማወቄ አስደስቶኛል። የተጠመቅኩት በ14 ዓመቴ ሲሆን አሁን 40 ዓመቴ ነው። ከመጠመቄ ከጥቂት ጊዜ በፊት አንስቶ ከመጠበቂያ ግንብ ወይም ከንቁ! መጽሔቶች ላይ የተወሰኑ ገጾችን በየቀኑ የማንበብ ልማድ አዳብሬ ነበር። መንፈሳዊነቴን መጠበቅ የቻልኩትም ሆነ ሳላነበው ያስቀመጥኩት ጽሑፍ የሌለኝ እንዲህ ያለ ልማድ በማዳበሬ እንደሆነ ይሰማኛል።

ኤስ. ኦ.፣ ጃፓን

እውነትን ለማግኘት ብቻውን የደከመው ማይክል ሰርቪተስ (ግንቦት 2006) ለዚህ ጠቃሚ የሆነ ጽሑፍ አመሰግናለሁ። ይበልጥ በስብከቱ ሥራ እንድቀጥልና ለይሖዋ ስም ጥብቅና እንድቆም አበረታቶኛል።

ኤም. አር.፣ ብራዚል

ብዙዎች ሰርቪተስን የሚያውቁት በሕክምናው መስክ ባተረፈው ስም ነው። ነገር ግን ይህ ርዕስ ሰርቪተስ ልበ ቅንና እውነትን ለማግኘት ብርቱ ጥረት ያደረገ ምሁር መሆኑን ጨምሮ ስለ እርሱ ሌሎች አስደናቂ ነገሮችን አሳውቆናል። ይህንን ርዕስ ስላወጣችሁ አመሰግናለሁ።

ኤም. ጄ.፣ ስፔን

ማስጠንቀቂያ መስማት ሕይወትን ያድናል (ሰኔ 2006) የይሖዋ አፍቃሪ ድርጅት ክፍል መሆን በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው። ካትሪና በተባለችው አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ቤቴን በመጠገን ለረዳችሁኝ ወንድሞችና እህቶች ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጽ እፈልጋለሁ። ይህ ቤት ለፍቅራቸው ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

አይ. ኤፍ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ሐርተወዳዳሪ የሌለው ምርጥ ክር (ሰኔ 2006) ከልጅነቴ ጀምሮ ሐር የሚሠራው እንዴት እንደሆነ እጠይቅ ነበር። ይህንን ርዕስ በንቁ! መጽሔት ላይ ሳየው በጣም የተደሰትኩ ሲሆን በደንብ አንብቤዋለሁ። ጽሑፉ ለይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ያለኝን አድናቆት ጨምሮልኛል።

ኤ.ኬ.ኤል.፣ ብራዚል

የአደገኛ ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶች (ሰኔ 8, 2005 እንግሊዝኛ) በዚህ ርዕስ ላይ በቀረቡት ፎቶዎች በመጠቀም ራሴን ስመረምር በቆዳዬ ላይ ወደ አደገኛ ካንሰርነት በመቀየር ላይ ያለ ጠቆር ያለ እብጠት አገኘሁ። ደግነቱ ካንሰሩ ገና ሥር መስደድ ሳይጀምር በቀዶ ሕክምና ወጣልኝ። ተግባራዊ ጠቀሜታ ላለው ለዚህ ዓይነቱ ትምህርት ይሖዋን ከልብ አመሰግናለሁ።

ኬ. ኤን.፣ ጃፓን