በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ገንዘብን ማሳደድ ጤንነትህን እያቃወሰው ነው?

ገንዘብን ማሳደድ ጤንነትህን እያቃወሰው ነው?

ገንዘብን ማሳደድ ጤንነትህን እያቃወሰው ነው?

በነገው ዕለት ባለጸጋ ብትሆን ምን ታደርጋለህ? ሩጫ ያልበዛበት ሕይወት በመምራት ዘና ብለህ መኖር ትጀምራለህ? ሥራህን ትተህ ከቤተሰብህና ከጓደኞችህ ጋር ከቀድሞው የበለጠ ጊዜ ታሳልፋለህ? በምትወደው የሥራ መስክ ትሰማራለህ? የሚገርመው ነገር ሀብታም የሆኑ ብዙ ሰዎች እንዲህ ያሉትን ነገሮች አያደርጉም። በዚህ ፈንታ አዲሱ አኗኗራቸው ያስከተለውን ዕዳ ለመክፈል ወይም ከበፊቱ ይበልጥ ሀብታም ለመሆን ሲሉ ቀሪውን ሕይወታቸውን ተጨማሪ ገንዘብ በማሳደድ ያሳልፉታል።

ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነት አካሄድ የተከተሉ አንዳንድ ሰዎች ፍቅረ ነዋይ በጤናቸው፣ በቤተሰብ ሕይወታቸውና በልጆቻቸው ሥነ ምግባር ላይ ያደረሰውን ጉዳት እየተመለከቱ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጻሕፍት፣ በመጽሔቶችና በጋዜጦች ላይ የሚወጡ ርዕሶች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና ቪዲዮዎች ከመጠን ያለፈ ቅንጦት የሚያስከትለውን አደጋ በማስጠንቀቅ ሰዎች በምትኩ “ቀለል ያለ አኗኗርን” እንዲመርጡ እያበረታቱ ነው። በርካታ ምንጮች እንዳመለከቱት ቁሳዊ ነገሮችን በማሳደድ መጠመድ አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ጤንነትህን ሊያቃውሰው እንዲሁም በስሜትህ ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

እርግጥ ነው፣ ሰዎች ፍቅረ ነዋይ ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ማሰብ የጀመሩት በዚህ ዘመን አይደለም። ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ብሎ ነበር:- “ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ። ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው፤ አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጒጒት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።”—1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10

ታዲያ ይህ እውነት ነው? ገንዘብንና ቁሳዊ ነገሮችን ማግኘት በሕይወታቸው ውስጥ ተቀዳሚ ግባቸው እንዲሆን ያደረጉ ሰዎች በእርግጥ ሥቃይ ይደርስባቸዋል? ወይስ ሀብት፣ ጤንነትና ደስተኛ ቤተሰብ ይኖራቸዋል? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ በሚቀጥለው ርዕሰ ትምህርት ላይ እንመልከት።