ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት?
ሕይወት እንዴት ተገኘ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት?
በኢስቶኒያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ከላይ የተጠቀሰውን ርዕስ የያዘውን መጽሐፍ ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን አስተዋውቀው ነበር። አንድ ወንድም እንዲህ ሲል ሪፖርት አድርጓል:- “በከተማችን ውስጥ የሚገኙትን በሩስያ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥባቸውን ትምህርት ቤቶች በሙሉ ጎብኝተን ነበር። እያንዳንዱ ትምህርት ቤት ለባዮሎጂ አስተማሪው ቢያንስ አንድ መጽሐፍ የወሰደ ሲሆን አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከ15 እስከ 40 የሚሆኑ መጻሕፍት እንዲመጣላቸው ጠይቀዋል።”
የአንድ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አድናቆቷን እንዲህ በማለት ጽፋለች:- “ሕይወት የተገኘው በፍጥረት መሆኑን ለመደገፍ የቀረቡት ግልጽ የሆኑ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች በጣም አስገርመውኛል። መጽሐፉ በሐቅ ላይ የተመሠረተና ውብ ሥዕሎችን ያካተተ ነው። መጻሕፍቱን በትምህርት ክፍለ ጊዜ ላይ የምንጠቀምበትን ወቅት በጉጉት እየተጠባበቅን ነው።”
እርስዎም ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።