በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰባችሁ የሚመራባቸውን ግልጽ ደንቦች አውጡ፤ እነዚህንም ከማስፈጸም ወደኋላ አትበሉ

ቤተሰባችሁ የሚመራባቸውን ግልጽ ደንቦች አውጡ፤ እነዚህንም ከማስፈጸም ወደኋላ አትበሉ

4

ቤተሰባችሁ የሚመራባቸውን ግልጽ ደንቦች አውጡ፤ እነዚህንም ከማስፈጸም ወደኋላ አትበሉ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በጆርጂያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሕይወት ባለሙያ የሆኑት ሮናልድ ሲመንስ እንዲህ ብለዋል:- “ለልጆች ግልጽ የሆኑ ደንቦች ማውጣትና እነዚህን ሲጥሱ በጥብቅ መቅጣት ለእነሱም የተሻለ ነው። እንደዚህ ዓይነት ጥብቅ ቅጣት የሚያስከትሉ ግልጽ ደንቦች ከሌሉ ልጆች ስለ ራሳቸው ብቻ የሚያስቡ፣ ራስ ወዳዶችና ደስታ የራቃቸው ስለሚሆኑ አብሯቸው ያለውን ሰው ሁሉ ያስመርራሉ።” የአምላክ ቃል “ልጁን . . . የሚወደው ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል” በማለት በግልጽ ይናገራል።—ምሳሌ 13:24

ተፈታታኝ የሚሆነው ለምንድን ነው? ለልጆቻችሁ ምክንያታዊ የሆኑ ገደቦች ማስቀመጥና እነዚህንም እንዲከተሉ ማድረግ ጊዜ፣ ጥረትና ጽናት ይጠይቃል። ልጆች ደግሞ በተፈጥሯቸው የሚወጣላቸውን ማንኛውንም ደንብ ለመቀበል ማንገራገር የሚቀናቸው ይመስላል። ሁለት ሴቶች ልጆችን በማሳደግ ላይ ያሉት ማይክና ሶኒያ “ልጆች የራሳቸው አእምሮና ፍላጎት እንዲሁም አብሯቸው የተወለደ ሕግ የመተላለፍ ዝንባሌ ያላቸው ትንንሽ ሰዎች ናቸው” በማለት ይህን ተፈታታኝ ሁኔታ ጠቅለል አድርገው ገልጸውታል። ማይክና ሶኒያ ሴት ልጆቻቸውን በጣም ይወዷቸዋል። ይሁን እንጂ “አንዳንድ ጊዜ ልጆች እልኸኛና ራስ ወዳድ ሊሆኑ ይችላሉ” በማለት ተናግረዋል።

መፍትሔው ምንድን ነው? ይሖዋ የእስራኤልን ብሔር የያዘበትን መንገድ ኮርጁ። አምላክ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር የገለጸበት አንዱ መንገድ፣ እንዲከተሏቸው የሚጠብቅባቸውን ሕግጋት በግልጽ ማስቀመጡ ነው። (ዘፀአት 20:2-17) የሰጣቸውን ሕግጋት አለመታዘዝ የሚያስከትለውን መዘዝም ነግሯቸው ነበር።—ዘፀአት 22:1-9

ስለዚህ ልጆቻችሁ ሊከተሏቸው እንደሚገባ የምታስቧቸውን ለቤተሰባችሁ ያወጣችኋቸው ሕጎች ወይም ደንቦች በጽሑፍ ልታሰፍሯቸው ትችላላችሁ። አንዳንድ ወላጆች እንዲህ ዓይነቱ ዝርዝር አንድ አምስት ያህል መመሪያዎችን የያዘ ሊሆን እንደሚችል ሐሳብ ያቀርባሉ። በጥንቃቄ የተመረጡና ያልተንዛዙ የቤተሰብ ደንቦችን ተከታትሎ ማስፈጸምም ሆነ ማስታወስ አስቸጋሪ አይሆንም። ከእነዚህ ደንቦች ጎን መመሪያዎቹን መጣስ የሚያስከትለውን ቅጣት ጻፉ። ቅጣቶቹ ምክንያታዊ መሆናቸውንና እናንተም ተግባራዊ ልታደርጓቸው ፈቃደኛ መሆናችሁን እርግጠኛ ሁኑ። እናትና አባትን ጨምሮ ሁሉም የቤተሰብ አባላት ምን እንደሚጠበቅባቸው እንዲያውቁ ደንቦቹን ዘወትር መመልከት ያስፈልጋል።

ልጆቹ ያወጣችኋቸውን ደንቦች ከጣሱ ወዲያውኑ ልትቀጧቸው ይገባል፤ ይህንንም የምታደርጉት በረጋ መንፈስ እንዲሁም ጥብቅ በሆነና ወጥነት ባለው መልኩ መሆን አለበት። ልጆቻችሁ ሲያበሳጯችሁ በምንም ዓይነት መልኩ እነሱን ከመቅጣታችሁ በፊት ንዴታችሁ እስኪበርድ መጠበቅ እንዳለባችሁ አስታውሱ። (ምሳሌ 29:22) ይሁን እንጂ ቅጣቱን ለሌላ ጊዜ አታስተላልፉት። እንዲሁም በቅጣቱ ረገድ አትደራደሩ። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ልጁ ደንቦቹን በቁም ነገር መመልከት እንደማያስፈልገው ይሰማዋል። ሁኔታው “በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል” ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር ይመሳሰላል።—መክብብ 8:11

የወላጅነት ሥልጣንህን ለልጆችህ በሚጠቅም መንገድ መጠቀም የምትችልበት ሌላ ምን መንገድ አለ?

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ፣ ‘አዎን’፤ አይደለም፣ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን።ማቴዎስ 5:37