በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤታችሁ ፍቅር የሰፈነበት እንዲሆን አድርጉ

ቤታችሁ ፍቅር የሰፈነበት እንዲሆን አድርጉ

2

ቤታችሁ ፍቅር የሰፈነበት እንዲሆን አድርጉ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ልጆች ፍቅር ይሻሉ፤ ፍቅር ካላገኙ ግን ይጠወልጋሉ። ስለ ሰው ልጅ አኗኗርና ባሕል የሚያጠኑት አሽሊ ሞንታጉ በ1950ዎቹ ዓመታት እንደሚከተለው በማለት ጽፈው ነበር:- “ለሰው ልጅ እድገት ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ምግብ ፍቅር ነው፤ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ጤንነቱ የተመካው ፍቅር በማግኘቱ ላይ ነው።” በዚህ ዘመን ያሉ ተመራማሪዎችም ሞንታጉ ከደረሱበት ድምዳሜ ጋር በመስማማት፣ “ልጆች በቂ ፍቅር አለማግኘታቸው በእድገታቸው ላይ ከባድ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር” ይናገራሉ።

ተፈታታኝ የሚሆነው ለምንድን ነው? ፍቅር በጠፋበትና ራስ ወዳድነት በሚንጸባረቅበት በዚህ ዓለም ውስጥ መኖር በቤተሰብ አባላት መካከል ያለው ግንኙነት ችግር እንዲኖረው ያደርጋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) ልጆችን ማሳደግ በባልና ሚስት ላይ የሚያስከትለው ገንዘብ ነክና ስሜታዊ ጫና ድሮውንም በትዳራቸው ውስጥ የነበረው ችግር እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀድሞውንም ቢሆን መግባባት ላቃታቸው ባልና ሚስት፣ ልጆቻቸው ሲያጠፉ በመቅጣትና ጥሩ ጠባይ ሲያሳዩ ደግሞ በመሸለም ረገድ የአመለካከት ልዩነት ሲፈጠር በመካከላቸው ያለው አለመግባባት ይበልጥ ሊባባስ ይችላል።

መፍትሔው ምንድን ነው? ቤተሰባችሁ አንድ ላይ ሆኖ የሚያሳልፈው ቋሚ ጊዜ መድቡ። ባልና ሚስትም ለብቻቸው ሆነው የሚጫወቱበት ጊዜ መመደብ ያስፈልጋቸዋል። (አሞጽ 3:3) ልጆቻችሁ ወደ መኝታቸው ከሄዱ በኋላ ያለውን ጊዜ ጥሩ አድርጋችሁ ተጠቀሙበት። እንዲህ ያሉትን ውድ ጊዜያት ቴሌቪዥን እንዲነጥቃችሁ አትፍቀዱለት። አንዳችሁ ለሌላው ያላችሁን ፍቅር ዘወትር በመግለጽ ፍቅራችሁ እንዳይቀዘቅዝ አድርጉ። (ምሳሌ 25:11፤ ማሕልየ መሓልይ 4:7-10) ሁልጊዜ ‘በደልን ከመከታተል’ ይልቅ በየቀኑ ለትዳር ጓደኛችሁ ያላችሁን አድናቆት የምትገልጹበትን መንገድ ፈልጉ።—መዝሙር 103:9, 10፤ ምሳሌ 31:28

ለልጆቻችሁም እንደምትወዷቸው ንገሯቸው። ይሖዋ አምላክ፣ ልጁን ኢየሱስን እንደሚወደው በግልጽ በመናገር ለወላጆች ምሳሌ ትቶላቸዋል። (ማቴዎስ 3:17፤ 17:5) በኦስትሪያ የሚኖር ፍሌክ የሚባል አንድ አባት እንዲህ ብሏል:- “ልጆች በተወሰነ መጠን እንደ አበቦች ናቸው። እነዚህ ትንንሽ ዕፅዋት ብርሃንና ሙቀት ለማግኘት ፊታቸውን ወደ ፀሐይ እንደሚያዞሩ ሁሉ ልጆችም ወላጆቻቸው ፍቅር እንዲያሳዩአቸውና ተፈላጊ የቤተሰቡ አባሎች መሆናቸውን እንዲያረጋግጡላቸው ይፈልጋሉ።”

ያገባችሁም ሆናችሁ ነጠላ ወላጆች፣ የቤተሰባችሁ አባላት እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱና ለአምላክ ፍቅር እንዲያዳብሩ ከረዳችኋቸው የቤተሰብ ሕይወታችሁ ይሻሻላል።

ይሁንና የአምላክ ቃል የወላጅነት ሥልጣንን ስለ መጠቀምስ ምን ይላል?

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት።ቈላስይስ 3:14