በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

የአንድ ልጅ እምነት (ነሐሴ 2006) ደስቲንን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች የሞቱ ሰዎች በቅርቡ በሚመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ በወጣትነት ጉልበታቸው ሲቦርቁ ለማየት እናፍቃለሁ።

ኤ. ኤ.፣ ስሪ ላንካ

ደስቲን ያለው እምነትና ድፍረት ልቤን በጥልቅ ነክቶታል። የእሱ ተሞክሮ፣ እውነት በሕይወቴ ውስጥ ያለውን ቦታ እንድመዝንና ቅድሚያ የምሰጣቸውን ነገሮች እንዳስተካክል ረድቶኛል። ከይሖዋ ጋር የመሠረትኩትን ጥሩ ዝምድና መጠበቅና የመንግሥቱን ጉዳዮች ማስቀደም በሕይወቴ ውስጥ ትልቁን ቦታ መያዝ እንደሚኖርባቸው ተገንዝቤያለሁ።

ኤም. ኬ. ቪ.፣ ብራዚል

ደስቲን ለእውነት በነበረው የአድናቆት ስሜት ልቤ ተነክቷል። ይህ ስሜቱ እኔንም ለሥራ አንቀሳቅሶኛል። ደስቲን ያደረጋቸው ነገሮች ይሖዋን ማስደሰትና ሌሎችን ማገልገል እንደሚፈልግ ያሳያሉ። እንደ ደስቲን ሁሉ እኔም ‘ሃይማኖቴን መጠበቅና ሩጫዬን መጨረስ’ እፈልጋለሁ!

ኤም. ኤን.፣ ጃፓን

ሰባት ዓመቴ ነው። ይህንን ተሞክሮ በማውጣታችሁ አመሰግናችኋለሁ። ደስቲን ከባድ ሕመም ቢኖርበትም በይሖዋ ላይ የነበረው ጠንካራ እምነት አስገርሞኛል። የእሱ ምሳሌ አምላክን ይበልጥ እንዳገለግል አበረታቶኛል።

ቲ. ዲ.፣ ጣሊያን

በዕፅዋት ላይ የሚታዩ አስደናቂ ንድፎች (መስከረም 2006) ይህ ርዕስ አንድ ሰዓት ተኩል ለሚያህል ጊዜ ትኩረቴን ስቦት ነበር። ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ርዕስ ነው! ትምህርቱን ይበልጥ ለመረዳት እንዲያስችለኝ አንዳንድ ሥዕሎችን ስዬ ነበር። ይሁን እንጂ የአንድን ሙሉ ክብ ወርቃማ ማዕዘን ይበልጥ የሚገልጸው 13/21 የሚለው ክፍልፋይ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሙሉው ክብ ቀሪ ክፍል ማለትም 222.5 ዲግሪ ነው።

ኤል. ኬ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የንቁ መጽሔት አዘጋጆች ምላሽ:- በርካታ አንባቢያን የአንድ ሙሉ ዙር ወርቃማ ማዕዘን ወደ 222.5 ዲግሪ የተጠጋ መሆኑን ተናግረዋል። ታዲያ በዚህ ርዕስ ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ የተለካውን በመጥቀስ ወርቃማው ማዕዘን 137.5 ዲግሪ እንደሆነ ተደርጎ የተገለጸው ለምንድን ነው? ዘ ዌብ ሪሶርስ ማትዎርልድ እንዲህ ይላል:- “ወርቃማው ማዕዘን አንድን ሙሉ ክብ [360°] ምንም ቦታ ሳያባክን የሚከፋፍል ማዕዘን ነው (ይሁን እንጂ ማዕዘኑ ከ180° ያነሰ እንዲሆን ሲባል በተቃራኒው አቅጣጫ መለካት ይኖርበታል)።” እንግሊዛዊው የሒሳብ ሊቅ ዶክተር ሮን ናት የሒሳብ ሊቃውንትና ሳይንቲስቶች ወርቃማውን ማዕዘን በዚህ መንገድ የሚለኩት ለምን እንደሆነ ሲያብራሩ “የሚቀናን በትንሹ ማዕዘን ላይ ‘ማተኮር’ ነው” ብለዋል። ምንም እንኳ ወርቃማው መጠን 13/21 ገደማ (ከግማሽ በላይ) ቢሆንም ወርቃማው ማዕዘን ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚገለጸው 137.5 ዲግሪ (ከግማሽ በታች) እንደሆነ ተደርጎ ነው።

“በእምነታቸው ምክንያት ታሰሩ” (ሚያዝያ 2006) የይሖዋ ምሥክር አይደለሁም፤ ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ የእናንተ ሃይማኖት አባላት የሆኑ ሰዎችን በጥልቅ እንዳላከብር አያግደኝም። በግሮስ ሮዛንና በቡከንዋልድ ማጎሪያ ካምፖች ውስጥ ታስሬ በቆየሁባቸው ጊዜያት ከበርካታ የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተዋውቄ ነበር። በምሳሌነት የሚጠቀሰው ጠባያቸው እንዲሁም ሃይማኖታዊ እምነታቸው ላቅ ያለ ስለነበር በዚያ በነበሩ እስረኞች ዘንድ ከበሬታና አድናቆት አትርፎላቸዋል። የናዚ ወታደሮች እንኳ በእነሱ ይገረሙ ነበር። የይሖዋ ምሥክሮች ቤቴ ቢመጡ ሁልጊዜ በደስታ እቀበላቸዋለሁ።

ፒ. ቪ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ