የርዕስ ማውጫ
የርዕስ ማውጫ
ሕዳር 2007
ልዩ እትም
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት መጣል ትችላለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ላይ በስፋት በመሰራጨት ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው መጽሐፍ ነው። ሆኖም በውስጡ የያዘው መልእክት የአምላክ መሆኑን እርግጠኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው? ታሪክንና ሳይንስን ጨምሮ ከተለያየ አቅጣጫ የቀረቡ ማስረጃዎችን እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።
5 በዓይነቱ ልዩ የሆነ መጽሐፍ
3. በውስጡ የያዘው ሐሳብ እርስ በርስ ያለው ስምምነት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረው ሐሳብ ሰዎች ያመነጩት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ እንዴት የአምላክ ቃል ነው ሊባል ይችላል?
12 መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ዘመናችን የደረሰው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ልጆች ዘንድ እጅግ ታዋቂ መጽሐፍ ለመሆን የበቃው እንዴት እንደሆነ ለመረዳት ይህን ርዕስ አንብብ።
15 የአርኪኦሎጂ ግኝቶች መጽሐፍ ቅዱስን ይደግፋሉ?
በዚህ ርዕስ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች ትክክለኛነት ስለሚያረጋግጡ አስደናቂ ቅርሶች ማንበብ ትችላለህ።
19 መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የሆነ ጭብጥ አለው። ጭብጡ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?
በዚህ ርዕስ ውስጥ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነገሩ አምስት የተሳሳቱ አመለካከቶች ሐሰት መሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ቀርበዋል።
23 መጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጠው ምክር ላይ እምነት መጣል ትችላለህ?
መጽሐፍ ቅዱስ የተሻለ ሕይወት እንድትኖር የሚያስችልህ ከመሆኑም በላይ ይበልጥ ደስተኛ እንድትሆን ሊረዳህ ይችላል። ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ይህን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች መከተል ያለብኝ ለምንድን ነው?
በርካታ ወጣቶች ለመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ከፍተኛ ግምት የሚሰጡት ለምን እንደሆነ አንብብ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጥሩ እንደሆነ ከሚነገርለት ከማንኛውም መጽሐፍ በእጅጉ ይበልጣል የምንለው ለምንድን ነው?
[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
© The Trustees of the Chester Beatty Library, Dublin
Musée du Louvre, Paris