ከሞት በኋላ ሕይወት—ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ከሞት በኋላ ሕይወት—ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ብዙዎች ከሞት በኋላ ይኖራል ተብሎ ስለሚታሰበው ሕይወት የተለያዩ ነገሮችን ሲማሩ ቆይተዋል። ይሁንና እነዚህ ትምህርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ብሎ አያስተምርም:-
▪ ጥሩ ሰዎች በሙሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ።
▪ የሞቱ ዘመዶቻችን ሊመለኩ ወይም አንዳንድ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ሊፈጸሙላቸው ይገባል።
▪ ሙታን በሕይወት ያሉ ሰዎችን ሊጎዱ አሊያም ሊጠቅሙ ይችላሉ።
▪ የሰው ልጆች የማትሞት ነፍስ አለቻቸው። በብዙ ሃይማኖቶች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው ይህ መሠረተ ትምህርት እንደ እሳታማ ሲኦልና ሪኢንካርኔሽን ላሉ ቅዱስ ጽሑፋዊ ላልሆኑ ትምህርቶች መፈጠር ምክንያት ሆኗል።
ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ አስደሳችና አጽናኝ የሆኑ ትምህርቶችን ይዟል። እነዚህ ትምህርቶች እዚህ ላይ በሚታየው መጽሐፍ ውስጥ ግልጽና ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው በሚችል መንገድ ተብራርተዋል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈለጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።