በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሸረሪት ድር

የሸረሪት ድር

ንድፍ አውጪ አለው?

የሸረሪት ድር

ክብደቱ ከጥጥ ጋር ሲወዳደር ቀለል ያለ ነው፤ ሆኖም ተመጣጣኝ መጠን ካለው ብረት ይጠነክራል። የሳይንስ ሊቃውንት ለአሥርተ ዓመታት ድር ፈታይ ሸረሪቶች የሚሠሩትን ድር ሲያጠኑ ቆይተዋል። እነዚህ ሸረሪቶች ከሚያደሯቸው ሰባት የድር ዓይነቶች ሁሉ እጅግ ጠንካራ የሆነው ድራግላይን የሚባለው ድር ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። ይህ ድር አብዛኛውን ጊዜ ለልብስ መሥሪያ ከሚያገለግለው የሐር ትል ፈትል ይልቅ ውኃ የመከላከል አቅም ያለው ከመሆኑም በላይ እጅግ ጠንካራ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ:- የጥይት መከላከያ ልብስ ለመሥራት እንደሚያገለግለው እንደ ኬቭላር ያሉ በፋብሪካ የሚሠሩ ክሮችን ለማምረት ከፍተኛ ሙቀትና ሕይወት ካላቸው ነገሮች የተሠሩ ማሟሚያዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። በአንጻሩ ሸረሪት ድሯን ለማድራት ከፍተኛ ሙቀት የማያስፈልጋት ሲሆን ለማሟሚያ የምትጠቀመው ደግሞ ውኃ ነው። ከዚህም በላይ ድራግላይን የሚባለው ድር ከኬቭላር የበለጠ ጠንካራ ነው። ከድራግላይን ድር የተሠራ መረብ አንድን ኳስ ሜዳ የሚሸፍን ስፋት እንዲኖረው ቢደረግ በመብረር ላይ ያለን አንድ ትልቅ አውሮፕላን ማስቆም ይችላል!

የድራግላይን ድር ጥንካሬ ተመራማሪዎችን ቢያስደምም ምንም አይገርምም። “የሳይንስ ሊቃውንት፣ ከጥይት መከላከያ አንስቶ ድልድይን ወጥሮ ለመያዝ እስከሚያገለግለው በጣም ወፍራም ሽቦ ድረስ ያሉ የተለያዩ ነገሮችን ለመሥራት እንደ ድራግላይን ድር ጠንካራ የሆነ ነገር መሥራት ይፈልጋሉ” በማለት አሚ ካኒንግሃም የተባሉ ሴት ሳይንስ ኒውስ በተባለው መጽሔት ላይ ጽፈዋል።

ይሁን እንጂ የድራግላይን ድር የሚሠራው በሸረሪቷ ሰውነት ውስጥ በመሆኑና ሂደቱንም ገና ሙሉ በሙሉ መረዳት ስላልተቻለ ይህ ዓይነቱ ድር የሚሠራበትን መንገድ መኮረጅ ቀላል አይደለም። ኬሚካል ኤንድ ኢንጂነሪንግ ኒውስ በተባለው መጽሔት ላይ የተጠቀሱት ሸሪል ሃያሺ የተባሉ ባዮሎጂስት እንዲህ ብለዋል:- “በርካታ አዋቂዎች፣ በምድር ቤታችን ውስጥ ያሉት ሸረሪቶች በተፈጥሯቸው ሊሠሩት የሚችሉትን ነገር አስመስለው ለመሥራት እየጣሩ መሆናቸውን ማወቁ አቅማችን ውስን መሆኑን እንድንገነዘብ የሚያደርግ ነው።”

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ሸረሪትና እንደ ብረት የጠነከረ ድሯ በአጋጣሚ የተገኙ ናቸው ወይስ ድንቅ ችሎታ ያለው ፈጣሪ ሥራ ናቸው?

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሸረሪት ድር ስታደራ በአጉሊ መነጽር ሲታይ

[ምንጭ]

Copyright Dennis Kunkel Microscopy, Inc.