በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ

ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ

ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ

እንዲህ ሊባልለት የሚችለው የትኛው መጽሐፍ ይመስልሃል? በኮሎራዶ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ስለያዛቸው ቁም ነገሮችና ዛሬ እያንዳንዱ ሰው ሊያነበው የሚገባ ጠቃሚ መጽሐፍ የሆነው ለምን እንደሆነ የሚያብራራ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ የተባለ ብሮሹር ደረሳት። ለብሮሹሩ ያላትን አመስጋኝነት ለመግለጽ የሚከተለውን አጭር ደብዳቤ ጽፋለች:-

“በአጭር አነጋገር በብሮሹሩ ተደስቻለሁ። እስከ መጨረሻው አንብቤዋለሁ። እንዲያውም አንዴ ማንበብ ከጀመርኩ በኋላ ማቆም አልቻልኩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር እንደማይጋጭ የሚያሳይ በጣም ጥሩ የሆነ ግንዛቤ በማስጨበጥ የአምላክን ቃል ዋና ዋና ሐሳቦች ጎላ አድርጎ ይገልጻል። ብሮሹሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉም ሰው እንዲያነበው ለማድረግ ሲባል እንዴት እንደተተረጎመ እንዲሁም እስከ ዘመናችን ተጠብቆ የቆየው እንዴት እንደሆነ ይናገራል።”

በእርግጥም፣ መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ውስጥ ከሌላ ከማንኛውም መጽሐፍ ይልቅ በስፋት የተሰራጨ በመሆኑ እስከ ዛሬ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ የሚበልጥ እጅግ አስደናቂ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀው ከ2,000 ዓመታት ገደማ በፊት ቢሆንም እንኳ ከሳይንስ ጋር ፈጽሞ የማይጋጭ ከመሆኑም በላይ የያዛቸው ትምህርቶች በዘመናችንም ጠቃሚ መመሪያ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው።

አንተም ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ ይህን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር አንድ ቅጂ እንዲላክልህ መጠየቅ ትችላለህ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን ብሮሹር ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።