በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በታሪክ ውስጥ ከሁሉ የላቀ ግምት የተሰጠው ክንውን

በታሪክ ውስጥ ከሁሉ የላቀ ግምት የተሰጠው ክንውን

በታሪክ ውስጥ ከሁሉ የላቀ ግምት የተሰጠው ክንውን

ይህ ክንውን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ መሆኑ ሰዎች ለአምላክ ያላቸውን ታማኝነት መጠበቅ እንደሚችሉ በማሳየት የአምላክን ጻድቅነት አረጋግጧል።

ከዚህም ባሻገር ሰዎች ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ከፍቶላቸዋል።

በሞቱ ዋዜማ ምሽት ላይ አንድ ዝግጅት በማድረግ የሞቱን መታሰቢያ ያቋቋመው ኢየሱስ ራሱ ነው። ዝግጅቱ ቀለል ያለ ነበር። በዚያ ዝግጅት ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሏቸው ነበር።—ሉቃስ 22:19, 20

አንተስ በዚህ ታላቅ ክንውን መታሰቢያ ላይ ትገኛለህ?

የይሖዋ ምሥክሮች በታሪክ ውስጥ ከሁሉ የላቀ ግምት በሚሰጠው በዚህ ክንውን መታሰቢያ ላይ አብረሃቸው እንድትገኝ በአክብሮት ጋብዘውሃል። በዚህ ዓመት የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የሚከበረው ቅዳሜ መጋቢት 13, 2000 (March 22, 2008) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። ትክክለኛውን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ በአቅራቢያህ ወደሚገኝ የመንግሥት አዳራሽ ሄደህ መጠየቅ ትችላለህ። በዝግጅቱ ላይ ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም፤ ሰዎች ሁሉ በቦታው ተገኝተው የሚቀርበውን ትምህርት ሰጪ ንግግር እንዲያዳምጡና ቀለል ባለ ሁኔታ የሚዘጋጀውን ሥነ ሥርዓት እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል።