በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ሥዕሉን አብራራ

1. በማቴዎስ 25:31-46 ላይ በሰፈረው ዘገባ መሠረት “የሰው ልጅ” የተባለው ማን ነው?

ፍንጭ:- ማቴዎስ 16:13-17ን አንብብ።

․․․․․․․․․

2. አንድ ሰው ከበጎች ወይም ከፍየሎች እንዲፈረጅ የሚያደርገው ምንድን ነው?

․․․․․․․․․

3. በጎቹና ፍየሎቹ ምን ይሆናሉ?

․․․․․․․․

ለውይይት:-

በዚህ ዘገባ ውስጥ “ወንድሞቼ” ተብለው የተጠሩት እነማን ናቸው? እነሱን ለመርዳት ምን ልታደርግ ትችላለህ?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 3 በመጨረሻው ዘመን ዘባቾች ምን ይላሉ? 2 ጴጥሮስ 3:________

ገጽ 7 ጥፋት በድንገት የሚመጣው መቼ ነው? 1 ተሰሎንቄ 5:________

ገጽ 20 አንድ የቤተሰብ ራስ ለቤተሰቡ ቁሳዊ ነገሮችን ማቅረብ የሚገባው ለምንድን ነው? 1 ጢሞቴዎስ 5:________

ገጽ 28 በአኗኗራችን ምን ዓይነት ባሕርይ ለማሳየት መናፈቅ ይኖርብናል? ዕብራውያን 13:________ NW

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከኢየሱስ የዘር ሐረግ ክፍል የሚመደበው ማን ነው?

መልሱን ለማግኘት የሚያስችሉህን የሚከተሉትን ፍንጮች ልብ በል። ጥቅሶቹን አውጥተህ አንብብ፤ ከዚያም በተዘጋጀው ክፍት ቦታ ላይ ትክክለኛውን ስም ጻፍ።

4. ․․․․․․․․

ፍንጭ:- የአብርሃም ቅድመ አያት ነኝ።

ዘፍጥረት 11:24-26ን አንብብ።

5. ․․․․․․․

ፍንጭ:- ወደ ከነዓን ለመሄድ ቤተሰቤን ይዤ ከዑር ወጥቻለሁ።

ዘፍጥረት 11:31ን አንብብ።

6. ․․․․․․․

ፍንጭ:- ይሖዋ “የብዙ ሕዝቦች አባት” እንድሆን አስቦ ስሜን ቀይሮታል።

ዘፍጥረት 17:5ን አንብብ።

▪ መልሱ በገጽ 19 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. ኢየሱስ።

2. የኢየሱስን መንፈሳዊ ወንድሞች የሚይዝበት መንገድ።

3. በጎቹ የዘላለም ሕይወት ሲያገኙ፣ ፍየሎቹ ደግሞ ለዘላለም ይጠፋሉ።

4. ናኮር።—ሉቃስ 3:34

5. ታራ።—ሉቃስ 3:34

6. አብርሃም።—ሉቃስ 3:34