በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በወጣትነት የሚከሰትን የመንፈስ ጭንቀት መቋቋም

በወጣትነት የሚከሰትን የመንፈስ ጭንቀት መቋቋም

በወጣትነት የሚከሰትን የመንፈስ ጭንቀት መቋቋም

በሜክሲኮ ውስጥ የእንግሊዝኛ ትምህርት በመከታተል ላይ የነበሩ ተማሪዎች በመረጡት ርዕስ ላይ አንድ ንግግር ተዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ነበር። ማሪትሳ እንዲህ ትላለች:- “ለተወሰነ ጊዜ የመንፈስ ጭንቀት የነበረብኝ ሲሆን በመስከረም 2001 ንቁ! መጽሔት ላይ ‘በመንፈስ ጭንቀት ለሚሠቃዩ ወጣቶች የሚሆን እርዳታ’ በሚል ርዕስ የወጡት ተከታታይ ትምህርቶች ረድተውኛል። በመሆኑም በመጽሔቱ ውስጥ የቀረቡትን መረጃዎች በመጠቀም ንግግሬን ያቀረብኩ ሲሆን እጅግ በጣም ጥሩ የሚል ውጤት ተሰጠኝ። በኋላም ንቁ! መጽሔት ላይ የወጡትን ተከታታይ ርዕሰ ትምህርቶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ለተማሪዎቹና ለአስተማሪዎቼ ሰጠኋቸው።”

ከሁለት ዓመት በኋላ ማሪትሳ አገልግሎት ላይ ሳለች እሷ ከዚህ በፊት ወስዳው የነበረውን የእንግሊዝኛ ትምህርት በመከታተል ላይ ያለች አንዲት ተማሪ አገኘች። የሚገርመው ተማሪዋ፣ በንቁ! መጽሔት ላይ ወጥቶ የነበረውን በወጣትነት ስለሚከሰት የመንፈስ ጭንቀት የሚናገረውን ተከታታይ ርዕሰ ትምህርት ፎቶ ኮፒ ለማሪትሳ አሳየቻት። አስተማሪዋ ለእያንዳንዱ ተማሪ ይህን ተከታታይ ርዕሰ ትምህርት እያባዛች መስጠቷ ትልቅ ዋጋ እንደሰጠችው ያሳያል!

ወጣቶች ስለሚያጋጥማቸው የመንፈስ ጭንቀት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ መመልከት ይቻላል። መጽሐፉ ከያዛቸው ምዕራፎች መካከል “ራሴን የማልወደው ለምንድን ነው?”፣ “በጣም የምጨነቀው ለምንድን ነው?” እና “የብቸኝነት ስሜት እንዲለቀኝ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?” የሚሉት ርዕሶች ይገኙበታል። ይህን መጽሐፍ ለማግኘት ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች ውስጥ አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።