በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በይሖዋ መንፈስ በሚመራው ንጉሥ አማካኝነት የሚገኘውን በረከት እጨዱ”

“በይሖዋ መንፈስ በሚመራው ንጉሥ አማካኝነት የሚገኘውን በረከት እጨዱ”

“በይሖዋ መንፈስ በሚመራው ንጉሥ አማካኝነት የሚገኘውን በረከት እጨዱ”

‘ሰው ሰውን ለመጕዳት ገዥ ሆኗል።’ በመክብብ 8:9 ላይ የሚገኘው ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሰው አገዛዝ ያስመዘገበውን ታሪክ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የተሻለ ነገር ማድረግ እንችል ይሆን? ወይስ እንዳለፉት ጊዜያት ነገሮች በዚያው መንገድ ይቀጥላሉ? “በአምላክ መንፈስ መመራት” በሚል ጭብጥ በሚደረገው የ2008/2009 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ የሚቀርበው የሕዝብ ንግግር ለእነዚህ ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣል። “በይሖዋ መንፈስ በሚመራው ንጉሥ አማካኝነት የሚገኘውን በረከት እጨዱ” የሚል ርዕስ ያለው ይህ ንግግር፣ በእውነተኛ ፍትሕና በፍቅር በሚገዛው እንዲሁም ለእኛ ሲል ሕይወቱን በሰጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያተኮረ ይሆናል።—ማቴዎስ 20:28

ኢየሱስን ከሌሎች ገዥዎች ሁሉ የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው? የአምላክ ነቢይ የሆነው ኢሳይያስ እንዲህ በማለት መልሱን ይሰጠናል:- “የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኀይል መንፈስ፣ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም። ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል”—ኢሳይያስ 11:2-4

እርስዎስ ስለ ንጉሡ የተሰጠውን ይህን መግለጫ ማራኪ ሆኖ አግኝተውታል? እንግዲያው ከዚህ ወር ጀምሮ በዓለም ዙሪያ ከሚካሄዱት በመቶዎች ከሚቆጠሩ የአውራጃ ስብሰባዎች መካከል በአንዱ ላይ በመገኘት ይህን የሕዝብ ንግግር እንዲያዳምጡ ተጋብዘዋል። ስብሰባው በአቅራቢያዎ የሚካሄድበትን ቦታ ለማወቅ ከፈለጉ በአካባቢዎ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ማነጋገር አሊያም በገጽ 5 ላይ ከሰፈሩት አድራሻዎች አንዱን በመጠቀም ወደዚህ መጽሔት አዘጋጆች መጻፍ ይችላሉ። የመጋቢት 1, 2008 መጠበቂያ ግንብ መጽሔት ስብሰባው በኢትዮጵያ የሚደረጉባቸውን ቦታዎች ዝርዝር ይዞ ወጥቷል።