በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

መልስህ ምንድን ነው?

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

በመጀመሪያ ዘፍጥረት 19:15-17, 23-26ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ፤ እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን የጎደሉትን ነገሮች ቦታ ቦታቸው ላይ ሳል።

1. ․․․․․․

2. ․․․․․․

3. ․․․․․․

ለውይይት:-

የሎጥ ሚስት ምን ደረሰባት? ለምንስ? ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት አገኘህ?

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 6 ወላጆች ለምን ነገር ፈጣን መሆን ይገባቸዋል? ያዕቆብ 1:________

ገጽ 7 መረን የተለቀቀ ልጅ ምን ያደርጋል? ምሳሌ 29:________

ገጽ 10 አምላክ፣ ዓመፅን ስለሚወዱ ሰዎች ምን ይሰማዋል? መዝሙር 11:________

ገጽ 20 አምላክ ከምን ይልቅ ታላቅ መሆኑን እርግጠኞች መሆን እንችላለን? 1 ዮሐንስ 3:________

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

በኢየሱስ የዘር ሐረግ ውስጥ የሚመደበው ማን ነው?

መልሱን ለማግኘት የሚያስችሉህን የሚከተሉትን ፍንጮች ልብ በል። ጥቅሶቹን አውጥተህ አንብብ፤ ከዚያም በተዘጋጀው ክፍት ቦታ ላይ ትክክለኛውን ስም ጻፍ።

4. ․․․․․․

ፍንጭ:- ትዕማር ለይሁዳ ከወለደችለት መንታ ልጆች አንዱ ስሆን በእጄ ላይ ቀይ ክር አልታሠረልኝም።

ዘፍጥረት 38:24-30ን አንብብ።

5. ․․․․․․

ፍንጭ:- ሚስቴ ቀደም ሲል በኢያሪኮ ከተማ የምትኖር ጋለሞታ ነበረች።

ኢያሱ 2:1ን እና ማቴዎስ 1:5ን አንብብ።

6. ․․․․․․

ፍንጭ:- አንዲት ሞዓባዊት መበለት አግብቼ ነበር።

ሩት 4:9, 10ን አንብብ።

▪ መልሱ በገጽ 29 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. የሎጥ ሚስት።

2. የሎጥ የመጀመሪያ ልጅ።

3. የሎጥ ሁለተኛ ልጅ።

4. ፋሬስ።—ሉቃስ 3:33

5. ሰልሞን።—ሉቃስ 3:32

6. ቦዔዝ።—ሉቃስ 3:32