በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምድር የመጪዎቹን ትውልዶች መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅም ይኖራት ይሆን?

ምድር የመጪዎቹን ትውልዶች መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅም ይኖራት ይሆን?

ምድር የመጪዎቹን ትውልዶች መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅም ይኖራት ይሆን?

ካናዳ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

የሚሌኒየሙ ሥነ ምሕዳራዊ ግምገማ ተብሎ የተጠራው ጥናት ተካፋይ የነበሩት ምሁራን በዓለም ታላላቅ ሥነ ምሕዳራዊ ገጽታዎች ላይ አራት ዓመት የፈጀ ጥልቅ ጥናት ካደረጉ በኋላ የመጀመሪያ ሪፖርታቸውን ይፋ አድርገዋል። ከደረሱባቸው መደምደሚያዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል:- ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የምግብ፣ የንጹሕ ውኃ፣ የእንጨት፣ የክርና የነዳጅ ዘይት ፍላጎት ለማሟላት የተደረገው ጥረት በምድር ሥነ ምሕዳር ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ለውጥ አስከትሏል፤ ይህ ደግሞ ምድር የመጪዎቹን ትውልዶች መሠረታዊ ፍላጎት የማሟላት አቅሟን በእጅጉ ጎድቶታል። ምድር ሰብሎችን ለማራባት፣ በዱር ዕፅዋት አማካኝነት አየሩን ለማጣራትና በውቅያኖስ አማካኝነት አልሚ ንጥረ ነገሮችን እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል ባላት ተፈጥሯዊ ችሎታ ላይ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሯል። በተጨማሪም ፕላኔቷ ምድራችን በቅርቡ በርካታ የእንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎቿን ታጣለች የሚል ሥጋት አለ።

ግሎብ ኤንድ ሜይል የተሰኘ አንድ የካናዳ ጋዜጣ እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “ሰዎች ፕላኔቷ ምድራችንን ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ፍጥነት እያበላሿት በመሆኑ ምክንያት አንዳንድ ተፈጥሯዊ ሥርዓቶች በድንገት ከጥቅም ውጪ የመሆናቸው አጋጣሚ በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል፤ ይህ ደግሞ በሽታዎችን ሊያመጣ፣ የደን መመናመንን ሊያስከትል ወይም በባሕር ውስጥ የሚገኙ ሕይወት አልባ የሆኑ ቦታዎች እንዲበራከቱ ሊያደርግ ይችላል።” ጋዜጣው አክሎ እንዲህ ብሏል:- “ለሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ አስፈላጊ የሆነው አየር፣ ውኃና አልሚ ንጥረ ነገር እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችሉት ረግረጋማ ቦታዎች፣ ደኖች፣ በሣር የተሸፈኑ ሰፋፊ ምድሮች፣ የወንዝና የባሕር መገናኛዎች፣ በባሕር ዳርቻ የሚገኙ ዓሣ ማስገሪያ ጣቢያዎችና እነዚህን የመሳሰሉት ቦታዎች መልሶ ለመጠገን አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው።” ከላይ የተጠቀሰው የገምጋሚዎች ቡድን የዲሬክተሮች ቦርድ በምድር ሥነ ምሕዳር ላይ ያለውን ጫና የማርገቡ ኃላፊነት የወደቀው በኅብረተሰቡ ላይ መሆኑን የተስማማ ከመሆኑም በላይ ይህን ከግብ ለማድረስ “ሰው ተፈጥሮን በሚይዝበት መንገድ ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግ” እንደሚኖርበት ተናግረዋል።

ፕላኔቷን ምድራችንን ማዳን ይቻል ይሆን? የዚህ ጥያቄ መልስ ‘እንዴታ!’ የሚል ነው። የአምላክን ፍጥረታት የመጠበቅ ኃላፊነት በአደራ የተሰጠን እንደመሆናችን መጠን ተፈጥሮን ለመንከባከብ የቻልነውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። (መዝሙር 115:16) ይሁን እንጂ የምድር ሥነ ምሕዳር እንደገና ሚዛኑን እንዲጠብቅ ለማድረግ የግድ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል። ታላቁ ‘ፈጣሪያችን’ ምድርን ‘እንደሚጎበኛትና እጅግ እንደሚያበለጽጋት’ ቃል ገብቷል። (ኢዮብ 35:10፤ መዝሙር 65:9-13) ይህ ተስፋ ባሕሮችንም ሆነ በውስጣቸው የሚገኙትን ነገሮች ይጨምራል፤ ምክንያቱም ይሖዋ አምላክ ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን በባሕርም ላይ ሥልጣን አለው። (መዝሙር 95:5፤ 104:24-31) ደግሞም አምላክ ‘ስለማይዋሽ’ የሰጠው ተስፋ በሙሉ እንደሚፈጸም የተረጋገጠ ነው።—ቲቶ 1:2

ምድር የመጪዎቹን ትውልዶች መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል አቅም እንደሚኖራት ማወቁ እጅግ የሚያጽናና ነው። ይህ ሁኔታ ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ሰዎች ይሖዋን ወደር ስለማይገኝለት ጥበቡ፣ ኃይሉና ጥሩነቱ እንዲያወድሱት እንዲሁም ለፍጥረታቱ ስላሳየው ፍቅር እንዲያመሰግኑት ይገፋፋቸዋል።—መዝሙር 150:1-6

[በገጽ 12 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

መሬት:- NASA photo