በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በጣም ግሩም መጽሐፍ ነው!”

“በጣም ግሩም መጽሐፍ ነው!”

“በጣም ግሩም መጽሐፍ ነው!”

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ በተመለከተ ከላይ ያለውን አስተያየት የሰጡት በጋብቻ ዙሪያ የሚደረግን አንድ ጥናት በበላይነት የሚመሩ ሰው ናቸው። በጥናቱ ላይ የተካፈሉ አንድ ባልና ሚስት ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ማጥናታቸው ለትዳር ዝግጁ እንዲሆኑ እንደረዳቸው በመግለጽ የመጽሐፉን ቅጂ ለእኚህ ሰው ላኩላቸው።

ጥናቱን በበላይነት ይመሩ የነበሩት እኚህ ሰው ለተላከላቸው “ግሩም ስጦታ” ለማመስገን ለባልና ሚስቱ ደብዳቤ ጽፈዋል። ሰውዬው በደብዳቤያቸው ላይ እንደነዚህ ያሉ ባልና ሚስት “ትዳር ጠንካራና ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ ምን እንደሚያስፈልግ” ሌሎችን እንደሚያስተምሩ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። እኚህ ሰው ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለውን የመሰሉ ጽሑፎች በትዳር ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚረዱ እርግጠኛ ናቸው። የጥናቱ መሪ፣ እነዚህ ባልና ሚስት ጠንካራ እምነት ያላቸውና አምላክ እርዳታ እንደሚሰጣቸው ሙሉ በሙሉ የሚተማመኑ መሆኑ ጥቅም እንዳስገኘላቸው ገልጸዋል።

እኚህ ሰው፣ መጽሐፉን በዴስካቸው ላይ እንዳስቀመጡትና ተማሪዎቻቸው ጋብቻን አስመልክተው ምክር ሲጠይቋቸው እንደሚያሳዩዋቸው ተናግረዋል። ደብዳቤያቸውን ሲያጠቃልሉም “ይህን መጽሐፍ ከዚህ ቀደም በጭራሽ አይቼው አላውቅም፤ በጣም ግሩም መጽሐፍ ነው!” ብለዋል።

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ባልና ሚስቶችን ጠቅሟል። እርስዎም፣ የቤተሰብዎን ሕይወት ይበልጥ አስደሳች ሊያደርጉ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በሥራ ላይ እንዲያውሉ ሊረዳዎት ይችላል።

እርስዎም ይህን ባለ 192 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

□ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።