በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከንቁ! መጽሔት ያልታሰበ እርዳታ አገኘ

ከንቁ! መጽሔት ያልታሰበ እርዳታ አገኘ

ከንቁ! መጽሔት ያልታሰበ እርዳታ አገኘ

ቤኒን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው

የይሖዋ ምሥክር የሆነው የ23 ዓመቱ ኖኤል ትምህርቱን አቋርጦ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ በመሆን አብዛኛውን ጊዜውን በስብከት ለማሳለፍ ሲወስን ዘመዶቹ ራሱን ችሎ ለመኖር የሚበቃው ገንዘብ ማግኘት ስለመቻሉ ጥርጣሬ አድሮባቸው ነበር። እርግጥ ነው፣ ኖኤል አብዛኛውን ጊዜውን በስብከቱ ሥራ ለማሳለፍ እንዲችል በሳምንት ውስጥ የተወሰነ ሰዓት ብቻ የሚሠራበት ሥራ ለማግኘት ተቸግሮ ነበር። በመሆኑም በንቁ! መጽሔት ላይ “ሥራ ለማግኘት የሚረዱ አምስት ቁልፍ ሐሳቦች” የሚል ርዕስ ያለው ጠቃሚ ትምህርት ሲወጣ ኖኤል ትኩረት ሰጥቶ በተደጋጋሚ አነበበው። * ይህን ርዕስ ማንበቡ ረድቶት ይሆን? አዎን፣ እሱ ባሰበው መንገድ ባይሆንም ረድቶታል።

የአንድ የግል ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር፣ ኖኤልን ከቤት ወደ ቤት ሲሰብክ ተመለከተውና የይሖዋ ምሥክር እንደሆነ ጠየቀው። ርዕሰ መምህሩ ተጨማሪ አስተማሪ መቅጠር ፈልጎ ነበር። ይህ ሰው የይሖዋ ምሥክሮች ጥሩ አስተማሪዎች እንደሆኑ ያውቅ ስለነበር ኖኤልን አስተማሪ መሆን የሚፈልግ የይሖዋ ምሥክር ያውቅ እንደሆነ ጠየቀው። ኖኤል እንደማያውቅ ሲነግረው ርዕሰ መምህሩ “አንተስ አስተማሪ መሆን አትፈልግም?” አለው።

ኖኤል በአስተማሪነት ሠርቶ አያውቅም፤ በተጨማሪም ሲናገር አልፎ አልፎ የመንተባተብ ችግር አለበት። የቤኒን ትምህርት ቢሮ፣ አስተማሪ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች የመንተባተብ ችግር እንደሌለባቸው ለማረጋገጥ ፈተና እንዲፈተኑ መመሪያ ስላወጣ ሁኔታው ለኖኤል አስቸጋሪ ነበር። ርዕሰ መምህሩ “የምሥክር ወረቀቱን ማግኘት ከቻልክ በአስተማሪነት ትቀጠራለህ” በማለት ቃል ገባለት።

ኖኤል፣ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ሥልጠና ስላገኘ ጥሩ እድገት አድርጎ ነበር፤ ይህ ትምህርት ቤት በሕዝብ ፊት ንግግር የመስጠት ችሎታን ለማሻሻል የሚረዳ ሲሆን ሥልጠናው በይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ውስጥ በየሳምንቱ ይሰጣል። ኖኤል የንግግር ችሎታውን ስላሻሻለ በሚሰበሰብበት ጉባኤ ውስጥ የሕዝብ ንግግሮችን ማቅረብ እንኳ ችሎ ነበር። ያም ሆኖ ለፈተና በቀረበበት ወቅት በጣም ፈርቶ ነበር።

ፈተናውን የሚሰጠው ሰው ለኖኤል አንድ መጽሔት ሰጠውና በቀይ የተሰመረበትን አንቀጽ ጮክ ብሎ እንዲያነብ ጠየቀው። ኖኤል መጽሔቱ ላይ “ሥራ ለማግኘት የሚረዱ አምስት ቁልፍ ሐሳቦች” የሚለውን ርዕስ ሲመለከት ዓይኑን ማመን አቃተው። አንቀጹን ጥርት አድርጎ በማንበቡ የምሥክር ወረቀቱን ማግኘት ቻለ።

ፈተናውን የሚሰጠው ሰው በኋላ ላይ እንደገለጸው የይሖዋ ምሥክሮችን መጽሔቶች አዘውትሮ ያነባል። “እነዚህ መጽሔቶች ግንዛቤ የሚያሰፉና በጥሩ ሁኔታ የሚጻፉ በመሆናቸው አብዛኛውን ጊዜ ለፈተና እጠቀምባቸዋለሁ” በማለት ተናግሯል።

ኖኤል አስተማሪ ሆኖ መሥራት የጀመረ ሲሆን ርዕሰ መምህሩ በቀጣዩ ዓመትም እዚያው እንዲቀጥል ለማድረግ ፈልጎ ነበር፤ ኖኤል ግን ሌላ እቅድ ነበረው። በአገሩ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ እንዲያገለግል ተጋብዞ ነበር፤ ኖኤል በአሁኑ ጊዜ በዚያ እያገለገለ ነው።

[የግርጌ ማስታወሻ]