በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሲጋል እግር

የሲጋል እግር

ንድፍ አውጪ አለው?

የሲጋል እግር

▪ሲጋል የተባለው ወፍ በረዶ ላይ ቆሞም እንኳ ሰውነቱ አይቀዘቅዝም። ይህ ፍጡር የሰውነቱን ሙቀት ጠብቆ ማቆየት የቻለው እንዴት ነው? ሚስጥሩ ያለው እግሩ ውስጥ በሚካሄደው ሙቀት የማስተላለፍ ሂደት ላይ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ በሲጋል እግር ላይ ያለው የሞቀ ደም የሚተላለፍበት የደም ሥር የቀዘቀዘ ደም ከሚዘዋወርበት የደም ሥር ጋር ይነካካል። የሞቀውም ሆነ የቀዘቀዘው ደም በአንድ አቅጣጫ ቢፈስስ ኖሮ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚተላለፈው የሙቀት መጠን ግፋ ቢል ግማሽ ያህሉ ብቻ ይሆን ነበር። በተቃራኒ አቅጣጫ የሚፈስስ ከሆነ ግን ሙቀቱ መቶ በመቶ መተላለፍ ይችላል።

በሲጋል እግር ውስጥ የሚገኙት ሙቀት አስተላላፊዎች ወደ እግር የሚወርደውን ደም ሲያቀዘቅዙ ከእግር የሚመለሰውን ደግሞ ያሞቃሉ። የአእዋፍ ጥናት ሊቅ የሆኑት ጋሪ ሪችሰን በቀዝቃዛ አካባቢዎች የሚኖሩ አእዋፍን አስመልክተው ሲጽፉ ‘በሲጋል እግር ውስጥ የሚከናወነው እንዲህ ያለው ሙቀት የማስተላለፍ ሂደት በጣም ውጤታማና የረቀቀ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች የኃይል ብክነትን ለማስቀረት በምሕንድስና ውጤቶቻቸው ላይ ተጠቅመውበታል’ ብለዋል።

ምን ይመስልሃል? በሲጋል እግር ውስጥ የሚካሄደው ሙቀት የማስተላለፍ ሂደት እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ ንድፍ አውጪ አለው? *

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.6 እንዲህ ያለው ሙቀት የማስተላለፍ ሂደት በሌሎች እንስሳት፣ በሰዎችና በበርካታ የዓሣ ዝርያዎች ውስጥም ይካሄዳል።

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ/ሥዕሎች]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

በሲጋል እግር ውስጥ የሚገኙት ሙቀት አስተላላፊዎች ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም ያሞቃሉ

[ሥዕላዊ መግለጫ]

32°C

0-5°C

[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ሲጋል፦ © Michael S. Nolan/age fotostock